“የተቀናጀ የግብርና ልማት ለሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል  የሀዲያ ዞን ግብርና መምሪያ ወቅታዊ የተቀናጀ የግብርና ልማት ስራዎች ንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው

“የተቀናጀ የግብርና ልማት ለሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል  የሀዲያ ዞን ግብርና መምሪያ ወቅታዊ የተቀናጀ የግብርና ልማት ስራዎች ንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው

ሀዋሳ፡ ጥቅምት 14/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) “የተቀናጀ የግብርና ልማት ለሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል የሀዲያ ዞን ግብርና መምሪያ ወቅታዊ የተቀናጀ የግብርና ልማት ስራዎች ንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

የመድረኩ ዓላማ በዘርፉ እስካሁኑ በተከናወኑ ተግባራት ባጋጠሙ ችግሮችና ክፍተቶች በታዩ ጠንካራ ጎኖችና ምርጥ ተሞክሮዎች ላይ ያተኮረ ውይይት በማድረግ ቀጣይ ወቅታዊ የግብርና ተግባራት በስኬት እንዲጠናቀቁ ማስቻል ነው።

ወቅቱ በርካታ የግብርና ተግባራት የሚከናወኑበት በመሆኑ የመኸር ምርትን በወቅቱ መሰብሰብ፣ በቡናና ቅመማ ቅመም ልማትና ግብይት ስራዎች፣  የሌማት ትሩፋት ተግባራት፣ በበጋ መስኖ ተግባራት፣ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት በእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍና መሰል ተግባራት ላይ  ውይይት በማድረግ የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር የሚያስችል ውይይት እየተደረገ ይገኛል።

በቀጣይ በወረዳና በቀበሌ ደረጃ ተመሳሳይ መድረኮችን በማዘጋጀትና ውይይት በማድረግ ቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ የግብርናውን ዘርፍ በማዘመን በዘርፉ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ከምን ጊዜም በተሻለ ጠንካራ ስራ መስራትን ታሳቢ ያደረገ መድረክ ስለመሆኑም በሀድያ ዞን ግብርና መምሪያ ምክትል ኃላፊና የእርሻ ዘርፍ ኃላፊ በኩል የውይይት መነሻ ጽሑፍ በቀረበበት ወቅት ተመላክቷል።

በመድረኩም የሀድያ ዞን የመንግስት ረዳት ተጠሪና የፖለቲካና ርዕዮተ ዓለም ዘርፍ ኃላፊ አቶ ከይረዲን ራህመቶ፣ የዞኑን ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ እቴነሽ ሙሉጌታን ጨምሮ የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች፣ የግብርና መምሪያና የወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ማኔጅሜንት አካላት የየወረዳ አስተዳዳሪዎችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት በመሳተፍ ላይ ናቸው።

ዘጋቢ፡ ኤርጡሜ ዳንኤል – ከሆሳዕና ጣቢያችን