የመደመር ጉዞ በሚል ርዕስ የውይይት መድረክ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እየተካሄደ ነው
ሀዋሳ፡ ጥቅምት 14/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከኢትዮጽያ ዜና አገልግሎት ጋር በመተባበር የመደመር ጉዞ በሚል ርዕስ የተዘጋጀው የውይይት መድረክ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ በመካሄድ ላይ ነዉ ።
በውይይት መድረኩ ላይ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው፣ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም የሀይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች በውይይቱ መድረኩ ተገኝተዋል።
ሰለመደመርና አብይ ትርክት፣ የመደመር ዕሴት የፈጠረው ጸጋ ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች እና በሌሎችም የተለያዩ ጥናታዊ ጹሁፎች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው የውይይት መድረኩ በመምራት ላይ ሲሆኑ የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽ አማካሪ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ በመደመርና አብይ ትርክት ዙሪያ የውይይት መነሻ ጽሁፍ አቅርበዋል፡፡
የመደመር ዕሳቤን ላይ ግንዛቤ በመፍጠር ሀገራዊ መግባባትን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሻገር እንዲረዳ ታሳቢ ያደረገ መድረክ መሆኑ ተገልጿል ።
ዘጋቢ:- ፋሲል ሀይሉ
More Stories
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ
በሀዲያ ዞን ከ8መቶ 50ሺህ በላይ የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት መከናወናቸው ተገለፀ