21ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓልን ለማክበር አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የጌዴኦ ዞን ምክር ቤት አስታወቀ

21ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓልን ለማክበር አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የጌዴኦ ዞን ምክር ቤት አስታወቀ

‎

‎በዓሉን የአቅመ ደካሞችን ቤት መጠገንን ጨምሮ በሌሎች ሰብአዊ ድጋፍ የማድረግ ተግባራት በማከናወን እንደሚያከበርም ተገልጿል።

‎

‎የኢፌዴሪ ሕገ መንግስት የፀደቀበትና የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የእኩልነት መብት የታወጀበትን ህዳር 29 ቀን ለማስታወስ በመላ ሀገሪቱ ዕለቱ በተለያዩ ሁነቶች ይከበራ።

በዓሉ የሕዝብ ለሕዝብ ትስስርን ከማጠናከርም አልፎ የራሳቸውን ቱባ ባህል እንዲያስተዋውቁ ትልቅ ዕድል የሚፈጥር ነው።

‎

‎“በብዝሃነት የደመቀች፣ በምክክር የፀናች ስልጡን ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል 21ኛው የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል በድምቀት ለማክበር ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የጌዴኦ ዞን ምክር ቤት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መስፍን አለማየሁ ተናግረዋል።

‎

‎የአቅመ ደካሞችን ቤት በማደስ፣ የደም ልገሳ በማድረግ፣ በአረንጓዴ አሻራ የተተከሉ ችግኞችን በመንከባከብ፣ የፅዳት ዘመቻና ስፖርታዊ ውድድር በማከናወን በዓሉን በድምቀት እንደሚያከብሩ አቶ መስፍን አስታውቀዋል።

‎

‎በዓሉ በዞኑ በሚገኙ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች፣ ሴክተር መስሪያ ቤቶች፣ በትምህርት ቤቶች፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ዲላ ክላስተር ቢሮዎችና በሌሎች ተቋማት እስከ ህዳር 19/2019 ዓ.ም በድምቀት እንደሚከበር ኃላፊው አብራርተዋል።

‎

‎ዘጋቢ፡ ውብሸት ኃ/ማርያም – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን