ማንቸስተር ዩናይትድ ካልቪን ባሴይን ማስፈረም ይፈልጋል!
አዲሱ የማንቸስተር ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ በመጪው የጥር የዝውውር መስኮት የቡድኑን የተከላካይ መስመር ለማጠናከር ካስቀመጧቸው ቀዳሚ ኢላማዎች መካከል የፉልሃሙ የመሃል ተከላካይ ካልቪን ባሴይ በግንባር ቀደምትነት መቀመጡ ተሰምቷል።
በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኦልድ ትራፎርድ ስራቸውን በይፋ የሚጀምሩት ፖቸቲኖ፣ ቡድኑን በፕሪሚየር ሊጉ ከወራጅ ቀጠና ስጋት ማውጣት ቀዳሚ የቤት ስራቸው ይሆናል።
ከዚህ ጎን ለጎንም በጥር ወር ክለቡን የሚቀላቀሉ ተጫዋቾችን የመለየት ስራ በአስቸኳይ የሚጀምሩ ሲሆን፣ የተከላካይ ክፍሉን ማጠናከር ዋነኛ ትኩረታቸው መሆኑ ተዘግቧል።
ማንቸስተር ዩናይትድ በኋላ መስመር ላይ የሚታይበትን የፈጣንነት ክፍተት ለመሙላት ባሴይ ትክክለኛው ሰው እንደሆነ አምኖበታል ተብሏል።
ተጫዋቹ ያለው አካላዊ ብቃት እና ጥንካሬም ለቡድኑ ትልቅ አቅም ይፈጥራል።
የ26 ዓመቱ ናይጄሪያዊ ተከላካይ ከመሃል ተከላካይነት በተጨማሪ በግራ መስመር ተከላካይነት መጫወት መቻሉ፣ በተደጋጋሚ በጉዳት ለሚሰቃየው ሉክ ሾው ጥሩ አማራጭ እንዲሆን ያደርገዋል።
ማንቸስተር ዩናይትድ በዘንድሮው የውድድር ዘመን በመጀመሪያዎቹ 10 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ብቻ 19 ግቦችን አስተናግዷል።
በሊጉ ከዩናይትድ በላይ ብዙ ግብ የተቆጠረባቸው ክሪስታል ፓላስ እና ኢፕስዊች ታውን ብቻ ናቸው።
በተጨማሪም ክለቡ በሁሉም ውድድሮች 30 ግቦችን በማስተናገድ በአውሮፓ አምስቱ ታላላቅ ሊጎች ከሚገኙ ክለቦች ሁሉ የከፋውን ሪከርድ ይዟል።
ይህም የክለቡ የመከላከል አቅም ምን ያኽል ደካማ እደሆነ ያሳያል።
ክለቡን ይህንን ድክመቱን በማስተዋል በጥር የዝውውር መስኮት የተከላካይ ክፍሉን ለማጠናከር በገበያው እንቅስቃሴ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
የቀድሞው የክለቡ ተከላካይ ጋሪ ኔቪልም ዩናይትድ “በፕሪሚየር ሊጉ እጅግ የደከመውን የተከላካይ መስመር የያዘ ቡድን ነው” ሲል በቅርቡ መተቸቱ ይታወሳል።
በአሰልጣኝ አልቫሮ አርቤሎአ ስር የፉልሃም አምበል በመሆን ድንቅ ብቃቱን እያሳየ የሚገኘው ባሴይ፣ በክለቡ ያለው ኮንትራት በመጪው ክረምት የሚጠናቀቅ ቢሆንም ፉልሃም ውሉን ለተጨማሪ 12 ወራት የማራዘም መብት አለው።
አሰልጣኝ አርቤሎአ ባሴይን “በፕሪሚየር ሊጉ ካሉ ምርጥ ተከላካዮች አንዱ ነው” ሲሉ ያሞካሹት ሲሆን፣ ክለቡ ረጅም ኮንትራት ሊያስፈርመው ፍላጎት እንዳለውም ገልጸዋል።
ይሁን እንጂ እስከ ጥር ወር ድረስ አዲስ ስምምነት ላይ መድረስ ካልተቻለ፣ ፉልሃም ከማንቸስተር ዩናይትድ የሚቀርብለትን ከፍተኛ የዝውውር ጥያቄ ውድቅ ማድረግ እንደሚከብደው ተነግሯል።
ባሴይ በዘንድሮው የውድድር ዘመን ፉልሃም በክሬቨን ኮቴጅ ከዩናይትድ ጋር አቻ በተለያየበት ጨዋታ ላይ ያሳየው ድንቅ እንቅስቃሴ የዩናይትድን ባለስልጣናት ትኩረት በእጅጉ እንደሳበ ተመልክቷል።
ዘጋቢ፡ሙሉቀን ባሳ
ማንቸስተር ዩናይትድ ካልቪን ባሴይን ማስፈረም ይፈልጋል!

More Stories
ዴክላን ራይስ በአርሰናል ቤት ለተጨማሪ ዓመታት የሚያቆየውን አዲስ ኮንትራት ለመፈረም ተስማማ
የዝውውር ጭምጭምታዎች አቋሜ ላይ ተጽዕኖ አሳድረዋል – ቪኒሺየስ ጁኒየር
ሮሜሉ ሉካኩ ከቤልጂየም ብሔራዊ ቡድን ራሱን ማግለሉን አስታወቀ