ሮሜሉ ሉካኩ ከቤልጂየም ብሔራዊ ቡድን ራሱን ማግለሉን አስታወቀ
የቤልጂየም ብሔራዊ ቡድን የምንጊዜም ኮከብ ግብ አስቆጣሪ የሆነው አጥቂ ሮሜሉ ሉካኩ፣ ከዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ጨዋታ ራሱን ማግለሉን በይፋ አስታውቋል።
ሉካኩ ይህንን ውሳኔውን ይፋ ያደረገው ሲሆን፣ ለዓመታት በቤልጂየም መለያ ያሳለፈውን ደማቅና ስኬታማ የእግር ኳስ ጉዞ በዚህ መልኩ ለመቋጨት መወሰኑ ተገልጿል።
የ33 ዓመቱ አጥቂ በብሔራዊ ቡድኑ ቆይታው የቤልጂየምን እግር ኳስ ወርቃማ ትውልድ ከመሩ ቁልፍ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ሲሆን፣ በዓለም ዋንጫ እና በአውሮፓ ዋንጫ መድረኮች ላይ ሀገሩን በመወከል አይረሴ ታሪኮችን ጽፏል።
በተለይም ለብሔራዊ ቡድኑ ያስቆጠራቸው በርካታ ግቦች በቤልጂየም እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ በቀዳሚነት ስሙ እንዲጠራ አድርገውታል።
ሮሜሉ ሉካኩ ከቤልጂየም ብሔራዊ ቡድን ጋር ባሳለፋቸው 16 ዓመታት ውስጥ 135 ጨዋታዎች አከናውኗል።
በነዚህ ጨዋታዎች 94 ጎሎችን በማስቆጠር የሀገሩ ብሔራዊ ቡድን የምንግዜም ከፍተኛው ጎል አስቆጣሪ ሆኖ ይገኛል።
በ4 የዓለም ዋንጫዎች እና በ3 የአውሮፓ ዋንጫዎች ላይ ለቤልጂዬም ተሰልፎ ተጫውቷል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ በአውሮፓ ውስጥ ከሚገኙ ወንዶች እግር ኳስ ተጫዋቾች መካከል 146 ጎሎችን ካስቆጠረው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በመቀጠል በታሪክ ሁለተኛው ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆን የክብረወሰን ባለቤት ሆኗል።
ቤልጂየም በፊፋ የዓለም ደረጃ ሰንጠረዥ አንደኛ ደረጃን እንድትይዝ እና በ2018 የዓለም ዋንጫ 3ኛ ደረጃን ይዛ እንድትጠናቀቅ ካደረጉት ወርቃማ ትውልድ መሪዎች ዋንኛዉ ነበር።
የሉካኩ ከብሔራዊ ቡድን መሰናበት ለቀያይ ሰይጣኖቹ አንድ ትልቅ ምዕራፍ መዘጋቱን የሚያሳይ ሲሆን፣ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የእግር ኳስ አፍቃሪያንና የቤልጂየም ደጋፊዎች ተጫዋቹ ለሀገሩ ላበረከተው ታላቅ አስተዋጽኦ ምስጋናቸውንና አድናቆታቸውን እየገለጹለት ይገኛሉ።
ዘጋቢ፡ሙሉቀን ባሳ
ሮሜሉ ሉካኩ ከቤልጂየም ብሔራዊ ቡድን ራሱን ማግለሉን አስታወቀ

More Stories
ዴክላን ራይስ በአርሰናል ቤት ለተጨማሪ ዓመታት የሚያቆየውን አዲስ ኮንትራት ለመፈረም ተስማማ
የዝውውር ጭምጭምታዎች አቋሜ ላይ ተጽዕኖ አሳድረዋል – ቪኒሺየስ ጁኒየር
ማንቸስተር ዩናይትድ ካልቪን ባሴይን ማስፈረም ይፈልጋል!