3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ይጠበቃል – የምስራቅ ጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያ

3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ይጠበቃል – የምስራቅ ጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን በበልግና በመኸር 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ ግብ ተጥሏል።

የዞኑ ግብርና መምሪያ ምክትልና የእርሻ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ሀይሉ ሰይፉ በዞኑ በመኸርና በበልግ ከለማው 73 ሺ 120 ሄክታር መሬት ላይ 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ ግብ ተጥሎ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል።

ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በምርት ላይ ጉዳት እንዳያደርስ የተቀናጀ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው ያሉት ምክትል ኃላፊው እስካሁን ከ56 ሺ ሄክታር በላይ ወይም 70 በመቶ በላይ እንደተሰበሰበ ገልፀዋል።

ለምርት አሰባሰብ ሂደት በ78 ኮምባይነ እንዲሁም በተደራጀ ማህበረሰብ ጉልበት ርብርብ እየተደረገ እንደሆነም ምክትል የመምሪያ ሀላፊው ተናግረዋል።

በዞኑ ከሚገኙ ወረዳዎች አንዱ በሆነው ሶዶ ወረዳ ነጥብ 8 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ ግብ መቀመጡን የወረዳው ግብርና ጽህፈት ቤት ምክትልና የእርሻ ዘርፍ ሃላፊ አቶ በከሬ ቱጂ ተናግረዋል።

በወረዳው 37 ሺ 889 ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች በበልግና በመኸር ተሸፍኖ በአሁኑ ወቅት የደረሱ ሰብሎችን በተቀናጀ ሁኔታ የመሰብሰብ ስራ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።

ከዚህም 1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ ግብ መቀመጡን ያነሱት አቶ በከሬ ይህ ግብ ወቅቱን ካልጠበቀ ዝናብና ከብክነት ለመታደግ በኮምባይነር የታገዘ ምርት አሰባሰብ ሂደት እየተከናወነ እንደሆነ ገልፀዋል።

ለወረዳው የተቀናጀ የምርት አሰባሰብ 45 የሚሆኑ ኮምባይነሮች ጥቅም ላይ መዋላቸውንም ተነግረዋል።

በወረዳው እስከ አሁን ከ27 ሺ ሄክታር በላይ መሬት ላይ የደረሰ ሰብል የተሰበሰበ ሲሆን ከዚህ ውስጥ በ17 ሺ ሄክታር መሬት ላይ የደረሰ ሰብል ተወቅቶ ከ820 ሺ ኩንታል በላይ ምርት ወደ ጎተራ ገብቷል ሲሉም አስረድተዋል።

አብዛኛው የስንዴ ልማት በክላስተር የሚካሄድ በመሆኑ በሜካናይዜሽን ምርትን በመሰብሰብ የምርት ጥራትና መጠንን ለማሳደግ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩንም አስታውቀዋል።

በወረዳው ውድገት ቀበሌ ነዋሪ ወጣት ማርቆስ ገነቴ ሁለት ሄክታር መሬት ላይ ያለማውን የስንዴ ምርት በኮምባይነር በመሰብሰብ ላይ እያለ ነበር ያገኘነው።

ኮምባነር በሚገባባቸው አካባቢዎች ላይ በኮምባይነር በሌሎች ማሳዎች ደግሞ በግልና በቡድን በመሆን ምርት እያሰባሰበ እንደሚገኝም ነው የተናገረው።

ዘጋቢ፡ መለሰች ዘለቀ