ከተሞችን ፅዱና ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ የጋራ ርብርብ እንደሚያስፈልግ ተገለፀ

ከተሞችን ፅዱና ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ የጋራ ርብርብ እንደሚያስፈልግ ተገለፀ

የሕብረተሰቡን  ሁለንተናዊ ተሳትፎ በማጠናከር ከተሞችን ፅዱና ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ የጋራ ርብርብ እንደሚያስፈልግ በአሪ ዞን የጂንካ ከተማ ማዘጋጃ ቤት አስታወቀ።

የከተማዋ ነዋሪዎች ንፁህ እና ጤናማ አከባቢን ለመፍጠር የሚያስችል የፅዳት  ዘመቻ አካሂደዋል።

በአሪ ዞን የጂንካ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት ኃላፊ ኢንጂነር ፈለቀ ወርቁ እንደገለፁት፤ የሕብረተሰቡን ተሳትፎ በማጠናከር ከተሞችን ፅዱና ምቹ ለማድረግ የጋራ ርብርብ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

በጂንካ ከተማ አስተዳደር የጤናዳም ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ገዛኸኝ ጌቶ በበኩላቸው፤ ውብና ማራኪ አከባቢን ለመፍጠር የግልና የአከባቢ ንፅህናን በንቃት መጠበቅ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

ጤንነቱ የተጠበቀ ዜጋን ለማፍራት፣ የአከባቢ ውበትን ለማረጋገጥ እና የአሪ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ ድሽታ ግና በዓል እሴት የሆነውን ፅዳትና ውበትን የዘወትር ተግባር እንደሚያደርጉ  በፅዳት ዘመቻው የተሳተፉ ነዋሪዎች አስረድተዋል።

ዘጋቢ፡ ተመስገን  አሰፋ –  ከጂንካ ጣቢያችን