ስፖርታዊ ውድድሮች የእርስ በርስ አንድነትን በማጠናከር ሕብረ ብሔራዊነትን ለማሳደግ እንደሚያግዙ የአሪ ዞን ባህልና ስፖርት ፅህፈት ቤት ገለፀ

ስፖርታዊ ውድድሮች የእርስ በርስ አንድነትን በማጠናከር ሕብረ ብሔራዊነትን ለማሳደግ እንደሚያግዙ የአሪ ዞን ባህልና ስፖርት ፅህፈት ቤት ገለፀ

በ2019 ዓ.ም 11ኛ ዙር የሚከበረውን የአሪ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫን ምክንያት በማድረግ በ10 ቡድኖች መካከል ድሽታ ግና ካፕ በጂንካ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።‎

ታህሳስ 1/2019 ዓ.ም የሚከበረውን የአሪ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ በዓል “ድሽታ-ግና” በአልን በማስመልከት በአሪ ዞን ባህልና ስፖርት ጽ/ቤት አዘጋጅነት እየተካሄደ ባለው የድሽታ-ግና ካፕ የእግር ኳስ ውድድር ወቅት መልክት ያስተላለፉት የአሪ ዞን ባህልና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መምህሩ ጌታቸው፤ ‎የቱሪዝም መዳረሻነትን ለማጎልበት ስፖርታዊ ሁነቶች የእርስ በርስ አንድነትን በማጠናከር ሕብረ ብሔራዊነትን ለማሳወቅ ያግዛል ብለዋል።

‎በውድድሩ 10 የእግር ኳስ ቡድኖች እየተሳተፉ እንደሆነ የ2019 የድሽታ ግና ካፕ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ይግረም ላቀው ገለጸው የስፖርቱንና የበዓሉን እሴት ለማረጋገጥ እየተሠራ መሆኑን አስረድተዋል።

በጂንካ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ሳይንስ ትምህርት ክፍል ሀላፊ አቶ ቢንያም ጌታቸው፥ ዩኒቨርሲቲው የስፖርት ሳይንስን በትምህርት ከመስጠት ባሻገር በድሽታ ጊና ካፕ በመሳተፍ ሀገር በቀል እሴቶችን ለማሳደግ ተግባራዊ ሥራዎችን እያከናወኑ እንዳለም አስገንዝበዋል።

ዘጋቢ፡ ተመስገን አሰፋ – ከጂንካ ጣቢያችን