ከተለያዩ ዞኖች የተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች በቤተሰብ እና በጎሳ ደረጀ የሚያደርጉት ባህላዊ የምርቃት ስርአት በየአካባቢው እና በሀገር ደረጀ አንድነትን፣ ፍቅርንና ሰላምን በማስፈን የመንግስትን የሰላም ግንባታ ግብ ከስኬት ለማድረስ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው የሀዲያ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ገለጸ።

ከተለያዩ ዞኖች የተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች በቤተሰብ እና በጎሳ ደረጀ የሚያደርጉት ባህላዊ የምርቃት ስርአት በየአካባቢው እና በሀገር ደረጀ አንድነትን፣ ፍቅርንና ሰላምን በማስፈን የመንግስትን የሰላም ግንባታ ግብ ከስኬት ለማድረስ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው የሀዲያ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ገለጸ።

በሀዲያ ዞን ሌሞ ወረዳ ሸቻና ሮማ ቀበሌ የሳመር መና ቤተሰብ ምረቃ ፕሮግራም ከተለያዩ ዞኖች የመጡ የሀገር ሽማግሌዎችና የሀዲያ ዞንና የሌሞ ወረዳ አመራሮች በተገኙበት ተካሂዷል።

በፕሮግራሙ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የሀዲያ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደመቀ በዶሬ እንደገለጹት፤ ከተለያዩ ዞኖች የተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች በቤተሰብ እና በጎሳ ደረጀ የሚያደርጉት ባህላዊ የምርቃት ስርአት በየአካባቢው እና በሀገር ደረጀ አንድነትን፣ ፍቅርንና ሰላምን በማስፈን የመንግስትን የሰላም ግንባታ ግብ ከስኬት ለማድረስ ከፍተኛ ድርሻ አለው።

ይህ ባህላዊ ዕሴት ለሀገር ሰላም ግንባታ ያለው ፋይደ ከፍተኛ በመሆኑ የአሁኑ ወጣቱ ትውልድ አጠናክሮ በማስቀጠል ለቀጣይ ትውልድ ማስተላለፍ አለበት ሲሉም አቶ ደመቀ አሳስበዋል።

ይህ ለማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ጠቃሚ የሆነ ባህል ተጠናክሮ እንዲቀጥል በመንግስት በኩል አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል ሲሉም አቶ ደመቀ ገልጸዋል።

በፕሮግራሙ ላይ ከተለያዩ ዞኖች የተገኙ የሀገር ሽማግሌዎች እንደገለጹት፤ የዚህ የባህላዊ የምረቃ ፕሮግራም ላይ የሚገኙ የሀገርና የባህል ዳኞች ከክፋት የተቆጠበ እና በመልካም ስነ-ምግባር የታነጸ ትውልድ እንዲፈጠር እና የተለያዩ ዞኖች የሽምግልና እና የአንድነት ባህል እንዲጠናከር የሚያስችል የልምድ ልውውጥ የሚደረግበት ነው።

በመሆኑም በየአካባቢያቸው የሚፈጠሩ ግጭቶችን በዕርቅ በመፍታት ለሀገር ሰላምና ልማት የሚቆም ትውልድ ለመፍጠር እየሰሩ መሆኑንም ገልጸዋል።

የሳመር መና ቤተሰብ ተወላጆችና የባህል ሽማግሌዎች በበኩላቸው የምረቃ ፕሮግራሙ ዋና ዓላማ የቤተሰቡ ተወላጆች እርስ በእርስ ለመተዋወቅ እና ከዞኑና አጎራባች ዞኖች ጋር የነበረውን አንድነትን በሰላምና ልማት የበለጠ ለማጠናከር መሆኑን ገልጸዋል።

ዘጋቢ: ሳሙኤል መንታሞ – ከሆሳዕና ጣቢያችን