ማክስ ዳውማን የጁድ ቤሊንግሃምን ክብረወሰን በመስበር ለእንግሊዝ ከ21 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የተጫወተ ትንሹ ተጫዋች ሆነ

ማክስ ዳውማን የጁድ ቤሊንግሃምን ክብረወሰን በመስበር ለእንግሊዝ ከ21 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የተጫወተ ትንሹ ተጫዋች ሆነ

የአርሰናል አካዳሚ ፍሬ የሆነው ታዳጊው ማክስ ዳውማን በ16 ዓመቱ ከ10 ወር ከ13 ቀኑ በመሰለፍ የእንግሊዝ ከ21 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድንን የወከለ በታሪክ በዕድሜ ትንሹ ተጫዋች በመሆን አዲስ ታሪክ ጽፏል።

ዳውማን ይህንን አስደናቂ ታሪካዊ ክብረወሰን የሰበረው፣ ከዚህ ቀደም በሪያል ማድሪዱ ኮከብ ጁድ ቤሊንግሃም ተይዞ የነበረውን ሪከርድ በማሻሻል ነው።

ታዳጊው የአማካይ ስፍራ ተጫዋች በእንግሊዝ እግር ኳስ ውስጥ በፍጥነት እያደጉ ካሉ ምርጥ ወጣት ባለተሰጥኦዎች መካከል አንዱ መሆኑን በዚህ ስኬቱ በድጋሚ አስመስክሯል።

በአርሰናል የወጣቶች አካዳሚ ውስጥ በሚያሳየው አስደናቂ ብቃት እና የኳስ ቁጥጥር ከፍተኛ አድናቆትን ያተረፈው ማክስ ዳውማን፣ ከዕድሜው በላይ በሆነ ብስለት በከፍተኛ ደረጃ መጫወት መቻሉ ለሀገሩ ከ21 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን እንዲመረጥ እና ይህን ታሪካዊ ዕድል እንዲያገኝ አስችሎታል።

የጁድ ቤሊንግሃምን ክብረወሰን መስበሩ ለወጣቱ ተጫዋች ትልቅ የሞራል ስንቅ ከመሆኑም ባለፈ፣ በቀጣይ ዓመታት ለአርሰናል ዋናው ቡድን እና ለእንግሊዝ ዋናው ብሔራዊ ቡድን ትልቅ ተስፋ የተጣለበት ተጫዋች መሆኑን አመላካች ነው ተብሏል።

ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ