የመደመር መንግስት ለጤናው ዘርፍ ትኩረት በመስጠቱ በ2018 በጀት አመት በልዩ ወረዳው ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል – የቀቤና ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ

የመደመር መንግስት ለጤናው ዘርፍ ትኩረት በመስጠቱ በ2018 በጀት አመት በልዩ ወረዳው ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል – የቀቤና ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ

የመደመር መንግስት ለጤናው ዘርፍ ትኩረት በመስጠቱ በ2018 በጀት አመት በልዩ ወረዳው ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን የቀቤና ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድአሚን በደዊ አስታወቁ፡፡

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቀቤና ልዩ ወረዳ ጤና ጽህፈት ቤት የ2018 አፈጻጸም ግምገማና የ2019 እቅድ ላይ ያተኮረ አመታዊ ጉባኤውን እያካሄደ ነው፡፡

የልዩ ወረዳው ጤና ጽ/ቤት “ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ለማህበረሰብ ተጠቃሚነት” በሚል መሪ ሀሳብ ከባለድርሻ አካላት ጋር የንቅናቄ መድረክ በወልቂጤ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል።

የቀቤና ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድአሚን በደዊ እንደገለፁት፤ የመደመር መንግስት ለጤናው ዘርፍ ትኩረት በመስጠቱ በ2018 በጀት አመት በልዩ ወረዳው ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል።

በተለይም በሽታን አስቀድሞ በመከላከል ላይ ትኩረት በማድረግ የእናቶችና ህጻናት ሞት ለመቀነስ እና ጤናው የተጠበቀ ማህበረሰብ ለመፍጠር እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

የቀቤና ልዩ ወረዳ ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ፋኪያ ኤሊያስ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት እንዳሉት፤ በ2018 በጀት ዓመት በጤናው ዘርፍ አበረታች ውጤት መመዝገቡን ገልጸዋል።

ለዚህ መሳካትም በየደረጃው ያሉ አመራሮች፣ የዘርፉ ባለሙያዎች እና ማህበረሰቡ ትልቅ ድርሻ እንደነበራቸውም አስረድተዋል።

በመድረኩ የ2018 አፈጻጸም ሪፓርት እና የ2019 እቅድ ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።

ዘጋቢ፡ አዱኛ ትዛዙ – ከወልቂጤ ጣቢያችን