የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) በተገኙበት የክልሉ የ2019 የትምህርት ጉባኤ በጂንካ ከተማ እየተካሄደ
“መፍጠር፣ መፍጠን እና መዝለል ከትምህርት ለትምህርት” በሚል መሪ ቃል ነው ጉባኤው እየተካሄደ ያለው።
ጉባኤው በክልሉ የትምህርት ልማት ስራዎች ተግዳሮትና ቀጣይ አቅጣጫ እንዲሁም የተማሪዎች ውጤት ማሻሻያና ማነቆዎችን በመለየት ችግሮቹን ለመፍታትና የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የሚያስችሉ የመፍትሔ ሃሳቦችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።
በጉባኤው ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አበባየው ታደሰ (ዶ/ር) እንዲሁም የክልልና የዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ዘጋቢ፡ ተመስገን አበራ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
ጠንካራ ተቋም በመመስረት ህዝብና መንግስት ከሴክተሩ የሚጠብቁትን ውጤት ለማስመዝገብ እንሰራለን – የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) የትምህርት ዘርፍ ስራ በተለመደ መልክ ሳይሆን በአዲስ መልክ የሚመራ መሆን አለበት ሲሉ ገለፁ
ጤናማ ማህበረሰብ አምራችና የልማት መሰረት በመሆኑ በክልሉ ጠንካራ የጤና ልማት ስርዓት መገንባት እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ገለጹ