ጠንካራ ተቋም በመመስረት ህዝብና መንግስት ከሴክተሩ የሚጠብቁትን ውጤት ለማስመዝገብ እንሰራለን – የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ

ጠንካራ ተቋም በመመስረት ህዝብና መንግስት ከሴክተሩ የሚጠብቁትን ውጤት ለማስመዝገብ እንሰራለን – የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ

ጠንካራ ተቋም በመመስረት ህዝብና መንግስት ከሴክተሩ የሚጠብቁትን ውጤት ለማስመዝገብ እንሰራለን ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ ኢሳ ገለጹ።

ቢሮው በአዲሱ አደረጃጀት መሠረት ወደ ሴክተሩ የተቀላቀሉ ሰራተኞች የትውውቅ እና የእንኳን ደህና መጣችሁ መድረክ በወልቂጤ ከተማ አካሔዷል።

ሰባተኛውን ሀገራዊ ምርጫ ተከትሎ የመደመር መንግስት ምስረታ መስከረም 23/2019 ዓ.ም በክልሉ ሲመሰረት የአስፈጻሚ አካላት ሥልጣንና ተግባር አደረጃጀት መወሰኛ አዋጅ መሠረት የሥራና ክህሎት ቢሮ በአዲስ መልክ መደራጀቱ ይታወቃል።

አደረጃጀቱ ከዚህ ቀደም በሥራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት፣ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና እና በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ በሦስት ቢሮዎች የነበሩ ተግባራትና ኃላፊነቶችን በአንድ ያደራጀ ነው።

በዚሁ አደረጃጀት መሠረት ወደ ሴክተሩ የተቀላቀሉ ሰራተኞች የትውውቅ እና የእንኳን ደህና መጣችሁ መድረክ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ ኢሳ፤ ሴክተሩ የተሰጠውን ግዙፍ ተልዕኮ ለመወጣት ትውውቁ መሰረታዊ ሚና አለው ብለዋል።

ህዝብና መንግስት ከሴክተሩ ብዙ ይጠብቃል ያሉት አቶ ሙስጠፋ፤ ለዚህም ጠንካራ ተቋም በመመስረት የሚጠበቅብንን ውጤት ለማስመዝገብ እንሰራለን በማለት ገልጸዋል።

የተቋሙ ሰራተኞች በበኩላቸው፤ ጥሩ ግንኙነት ለውጤታማ ስራ አፈጻጸም አጋዥ በመሆኑ ትውውቁ የቤተሰባዊነት ስሜት እንደሚፈጥር ተናግረዋል።

በሶስት የተለያዩ ተቋማት ይፈጸሙ የነበሩ ተግባራት ወደ አንድ መምጣታቸው ለአፈጻጸም ምቹና ለውጤታማነት አጋዥ መሆኑን ጠቁመው፤ ይህም በተናጥል የነበሩ ውጤቶች ይበልጥ ለማሳደግ ያስችላል ብለዋል።

ዘጋቢ፡ ተረፈ ሀብቴ – ከወልቂጤ ጣቢያችን