የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) የትምህርት ዘርፍ ስራ በተለመደ መልክ ሳይሆን በአዲስ መልክ የሚመራ መሆን አለበት ሲሉ ገለፁ
“መፍጠር፣ መፍጠን እና መዝለል ከትምህርት ለትምህርት” በሚል መሪ ቃል የክልሉ የትምህርት ጉባኤ እየተካሄደ ነው።
የትውልድ የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚወሰነው ዛሬ በትምህርት ላይ በምንሰራው ስራ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ የሀገሪቱ ብልጽግና ግብ ስኬቱም ይህ ነው ብለዋል።
የመድረኩ መዘጋጀት መሰረታዊ ዓላማ የጋራ ኃላፊነት ለመውሰድና ቀጣይ የሚታይ ውጤት ለማስመዝገብ ነው ሲሉ የዕለቱ የክብር ዕንግዳ የስራ መመሪያ ሰጥተው መድረኩን ከፍተዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህር ቢሮ ኃላፊ መስፍን መንዛ (ዶ/ር) በስልጣኔ ቁንጮ ላይ የተቀመጡ ሀገሮች ዋነኛ መነሻቸው ትምህርት ነው ብለዋል።
የትምህርት ውጤት ቀጣይነት ባለው መንገድ እንዲሻሻል መላው ህዝብ በሀላፊነት መንፈስ መስራት አለበት ሲሉ ተናግረዋል።
ባለፉት ዓመታት የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ አካላትን ዕውቅና መስጠትና ቀጣይ በትምህርት ልማት ላይ ከወትሮው በተለየ መልኩ ለመስራት መድረኩ መመቻቸቱንም ሀላፊው ገልፀዋል።
በጉባኤው ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉኤ ወ/ሮ ካሰች ኤልያስ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አበባየው ታደሰ (ዶ/ር) እንዲሁም የክልልና የዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ዘጋቢ፡ ተመስገን አበራ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
ጠንካራ ተቋም በመመስረት ህዝብና መንግስት ከሴክተሩ የሚጠብቁትን ውጤት ለማስመዝገብ እንሰራለን – የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) በተገኙበት የክልሉ የ2019 የትምህርት ጉባኤ በጂንካ ከተማ እየተካሄደ
ጤናማ ማህበረሰብ አምራችና የልማት መሰረት በመሆኑ በክልሉ ጠንካራ የጤና ልማት ስርዓት መገንባት እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ገለጹ