ኮቢ ማይኑ ወደ ልምምድ ተመለሰ

ኮቢ ማይኑ ወደ ልምምድ ተመለሰ

ማንችስተር ዩናይትድ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ከቼልሲ ጋር ለሚያደርገው ወሳኝ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ዝግጅት ላይ በሚገኝበት በዚህ ወቅት፣ ወጣቱ አማካይ ኮቢ ማይኑ ወደ ቡድን ልምምድ መመለሱ ተሰምቷል።

የ 21 ዓመቱ እንግሊዛዊው አማካይ፣ በዛሬው ዕለት በካሪንግተን የልምምድ ማዕከል ቡድኑ ባካሄደው የዝግጅት መርሃ ግብር ላይ ከቡድን አጋሮቹ ጋር ተሳትፏል።

የኮቢ ማይኑ ወደ ልምምድ መመለስ፣ ማንችስተር ዩናይትድ ቅዳሜ ዕለት ስታምፎርድ ብሪጅ ላይ ለሚያደርገው ወሳኝ ጨዋታ ለአሰልጣኝ ማይክል ካሪክ ትልቅ የኃይል መነቃቃት እንደሚፈጥር ይታመናል።

ማይኑ ከሳምንታት በፊት ዩናይትድ ከቶተንሃም ጋር 1 ለ 1 በተለያየበት ጨዋታ ላይ ጉዳት ካጋጠመው በኋላ፣ የቡድኑን አራት ተከታታይ ጨዋታዎች በጉዳት ምክንያት ላለማከናወን ተገዶ ነበር።

በዚህም በቻምፒየንስ ሊግ ከአትሌቲኮ ማድሪድ እና ከኮሞ እንዲሁም በፕሪሚየር ሊጉ ከሊድስ እና ከቦርንመዝ ጋር የተደረጉ ጨዋታዎች አምልጠውታል።


በሌላ በኩል፣ የማይኑ ወደ ልምምድ መመለስ ለአሰልጣኝ ማይክል ካሪክ መልካም ዜና ቢሆንም፤ የራሽፎርድ እና የሾው በዛሬው ልምምድ ላይ አለመገኘት ግን ተጨማሪ ስጋት ፈጥሯል።

በተለይም አጥቂው ማርከስ ራሽፎርድ በዳሌ ጉዳት ምክንያት ከሜዳ የራቀ ሲሆን፣ በተጨማሪም በብልት አካባቢ በሚሰማው የህመም ስሜት እየተሰቃየ እንደሚገኝ ታውቋል።

ሁለቱ ተጫዋቾች በሳምንቱ መጨረሻ በሚደረገው የቼልሲ ጨዋታ ላይ የመሰለፋቸው ነገር አጠራጣሪ ሆኗል።

ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ