በካራባኦ ካፕ አርሰናል ከሜዳው ውጪ ከፍሊትውድ ታውን ጋር ዛሬ ምሽት ይጫወታል
በእንግሊዝ ካራባኦ ካፕ ወደ ሩብ ፍፃሜ ለማለፍ በሚደረግ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ አርሰናል ከሜዳው ውጪ ፍሊት ውድን ዛሬ ምሽት 5 ሰዓት ላይ ይገጥማል።
ፍሊትውድ ታውን በእንግሊዝ 4ኛ የሊግ ዕርከን በሆነው ሊግ ቱ በመሳተፍ ላይ የሚገኝ ክለብ ነው።
በሊጉ 18ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ይህ ክለብ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በካራባው ካፕ 16 ውስጥ መግባት ችሏል።
ፍሊትውድ ከአርሰናል ጋር እንዲሁ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ ምሽት የሚገናኝ ይሆናል።
በፕሪሚዬር ሊጉ ከመሪው ማንቸስተር ሲቲ ጋር በነጥብ መስተካከል የቻለው አርሰናል ምሽት የሚገጥመው ፊሊትውድ ታውን በካራባኦ ካፕ የሚገጥመው 68ኛ እግርኳስ ክለብ መሆኑ ተገልጿል።
እንዲሁም መድፈኞቹ በእንግሊዝ 4ኛው የሊግ ዕርከን ከሆነ ክለብ ጋር ሲገናኙ ይህ ለ10ኛ ጊዜ መሆኑ ተመላክቷል።
በምሽቱ ጨዋታ በአርሰናል በኩል ዊሊያም ሳሊባ፡ሪካርዶ ካላፊዮሪ፣ቡካዮ ሳካ እና ክርስቶስ ዞሊስ በጉዳት ምክንያት የማይሰለፉ ተጫዋቾች ናቸው።
ወደ ሩብ ፍፃሜ ለማለፍ የሚደረጉ የሊግ ካፑ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች በነገው ዕለትም መካሄዳቸውን ሲቀጥሉ ሊቨርፑል ከቼልሲ እንዲሁም ማንቸስተር ሲቲ ከብራይተን የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ተጠባቂ ናቸው።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
በካራባኦ ካፕ አርሰናል ከሜዳው ውጪ ከፍሊትውድ ታውን ጋር ዛሬ ምሽት ይጫወታል

More Stories
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 4 ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ
አሰልጣኝ ቪንሰንት ኮምፓኒ በአምቡላንስ ወደ ሆስፒታል ተወሰዱ!
አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ የ10 ጨዋታዎች ቅጣት ተላለፈባቸው