አሰልጣኝ ቪንሰንት ኮምፓኒ በአምቡላንስ ወደ ሆስፒታል ተወሰዱ!

አሰልጣኝ ቪንሰንት ኮምፓኒ በአምቡላንስ ወደ ሆስፒታል ተወሰዱ!

የጀርመኑ ግዙፍ ክለብ ባየር ሙኒክ ዋና አሰልጣኝ ቪንሰንት ኮምፓኒ ከባድ የጤና ችግር አጋጥሟቸዋል።

ስካይ ስፖርት እንደዘገበው ከሆነ፣አሰልጣኙ በልልምድ ወቅት በድንገት የከባድ ህመም ሰለባ በመሆናቸው በአምቡላንስ ወደ ህክምና ተቋም ተወስደዋል።

ኮምፓኒ ከቀናት በፊት ከ አርሰናል ጋር ከተደረገው የ ዩፋ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ አስቀድሞ በቫይረስ መያዛቸው ይታወሳል።

በቫይረሱ መጠቃት ምክንያት በሰዎች ዘንድ ያልተለመዱ የእግር ህመሞች እና የዳሌ ችግሮች አጋጥመውት እንደነበር ተገልጿል።

የቀድሞው የማንችስተር ሲቲ ተከላካይ የነበሩት ኮምፓኒ፣ የአካል ጉዳቱና የህመም ስሜቱ እየበረታባቸውም ቢሆን ቡድኑን በሜዳ ላይ ለመምራት ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ቆይተዋል።

ይሁን እንጂ አካላቸው የሰጠውን የማስጠንቀቂያ ምልክት በአግባቡ ባለማዳመጣቸው እና ለዕረፍት በቂ ጊዜ ባለ መስጠታቸው አሁን ላይ ሁኔታው ተባብሶ ወደ ድንገተኛ ህክምና ደረጃ መድረስ እንደቻለ ተመላክቷል።

በአሰልጣኙ ጤና ዙሪያ የተፈጠረው ይህ ያልተጠበቀ ድንገተኛ ሁኔታ በባየር ሙኒክ ደጋፊዎችና የስራ አስፈፃሚዎች ዘንድ ትልቅ መደናገጥን ፈጥሯል።

ክለቡ የፊታችን ዕሁድ ከፍሬይቡርግ ጋር ለሚያደርገው የቡንደስሊጋ ጨዋታ እና ለቀጣይ መርሃ ግብሮቻቸው የኮምፓኒ መገኘት አጠራጣሪ መሆን የቡድኑን ስትራቴጂ የሚፈትን ትልቅ ፈተና ሆኗል።

የባየር ሙኒክ ደጋፊዎች እና የእግር ኳስ አፍቃሪያን አሰልጣኝ ቪንሰንት ኮምፓኒ ከህመማቸው አገግመው ወደ ስራ እንዲመለሱ ከፍተኛ ምኞታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።

ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ