የዳውሮ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 14ኛ ዓመት 12ኛ አስቸኳይ ጉባኤ  እየተካሄደ  ነው

የዳውሮ ዞን ምክር ቤት ባካሄደው 4ኛ ዙር 14ኛ የሥራ ዘመን 12ኛ አስቸኳይ ጉባኤ አቶ ትዕዛዙ ባዩን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾሟል።

የአዲሱን ዋና አስተዳዳሪ ሹመት ለምክር ቤቱ ያቀረቡት የክልሉ መንግሥት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪ የሆኑት አቶ አዝመራ አደም ናቸው።

ምክር ቤቱም የቀረበለትን ዕጩ ሹመት በሙሉ ድምፅ ያጸደቀ ሲሆን ተሿሚው አቶ ትዕዛዙ ባዩ በምክር ቤቱ አባላት ፊት ቀርበው ቃለ መሐላ በመፈጸም ኃላፊነታቸውን በይፋ ተረክበዋል።

 ዘጋቢ፡- እታገኝ  ዘነበ  ከዋካ  ቅርንጫፍ