አቶ ይሁን አሰፋ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የየም ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ

አቶ ይሁን አሰፋ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የየም ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የየም ዞን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዙር 14ኛ የስራ ዘመን 3ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን በሳጃ ከተማ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

ምክር ቤቱ እያካሄደ ባለው በዚህ አስቸኳይ ጉባኤው አቶ ይሁን አሰፋ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ በማድረግ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

ዋና አስተዳዳሪው በምክር ቤቱ ጉባዔ ፊት ቀርበው ቃለ መሀላ ፈፅመዋል።

ዘጋቢ፡ ጅላሉ ፈድሉ – ከወልቂጤ ጣቢያችን