አቶ መብራቴ ወልደማርያ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በመሆን ተሾሙ

አቶ መብራቴ ወልደማርያ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በመሆን ተሾሙ

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 14ኛ አመት 12ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን በወልቂጤ ከተማ እያካሄደ ባለበት ወቅት ነው አቶ መብራቴ ወልደማርያም ለጉራጌ ዞን አስተዳደር እጩ አድረጎ በምክር ቤቱ የጸደቀው።

አቶ መብራቴ ወልደማርያም በዞኑ በተለያዩ የስራ ዘርፎች በባለሙያነትና በአመራርነት ሲያገለግሉ በጥቂቱ በቀድሞው እነሞርና ኤነር ወረዳ በመምህርነት፣ በርእሰ መምህርነት፣ በሱፐርቫይዘርነት፣ የወረዳ አስተዳዳሪ አማካሪ በመሆን ሲያገለግሉ በዞን ደረጃ ደግሞ በጉራጌ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ምክትል ኃላፊ፣ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ እንዲሁም ያለፉትን ሶስት አመታት የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል።

ዘጋቢ፡ ዳዊት ዳበራ – ከወልቂጤ ጣቢያችን