የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) ከቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ጋር በጽህፈት ቤታቸው የስራ ርክክብ አደረጉ።
የቀድሞው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተደድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በርክክብ ስነስርዓቱ ወቅት እንደተናገሩት፤ በክልሉ የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች በተገቢው ተከናውነዋል።
የህዝብ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ስራዎችን በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች ማከናወን እንደተቻለም አክለው ገልጸዋል።
በቀጣይም ክልሉ በሚያከናውናቸው ተግባራት የድርሻቸውን እንደሚወጡም የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) አረጋግጠዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከምስረታ እስከ አሁን የነበረውን ጉዞ፣ የክልሉ መንግስት የ2019 በጀት አመት እቅድ እንዲሁም የክልሉን መንግስት የሰባት ዓመታት መሪ እቅድ ለአዲሱ ርዕሰ መስተዳድር አስረክበዋል።
አዲስ የተሰየሙት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) በበኩላቸው በክልሉ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ የልማት ስራዎች ውጤት የታየባቸውና ህዝብንም ተጠቃሚ ያደረጉ መሆናቸውን አንስተው፤ ይህንንም ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።
በመደመር እሳቤ በመመራት የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያጎለብቱ የልማት ስራዎችን ይበልጥ ማስፋትና ለስኬት ማብቃት እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ አስገንዝበዋል።
ኃላፊነት የህዝብና የመንግስት አደራ በመሆኑ የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከክልሉ ስራ አስፈፃሚ አካላት ጋር በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ዶ/ር የትምጌታ አመልክተዋል፡፡
ዶ/ር የትምጌታ አስራት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት በተካሄደው 7ኛ ዙር የምስረታ ጉባኤ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ከተሰየሙ በኋላ ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው በመገኘት የመንግሥት ሥራቸውን በይፋ ጀምረዋል።
ዘጋቢ:- በየነ ሰላሙ ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
ውብ፣ ጽዱና ለኑሮ ምቹ አካባቢን ለመፍጠር የደን ልማትና ጥበቃ ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባ የጉራጌ ዞን አስተዳደር ገለጸ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ በመሆን የተሾሙት አቶ መለሰ አለሙ የሥራ ርክክብ አደረጉ
ባህላዊ እሴቶችን የማልማት፣ የማበልፀግ እና የማስተዋወቅ ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ