ከ640 ሄክታር በላይ መሬት በካሳቫ መሸፈኑን በኮሬ ዞን የሳርማሌ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ
በኮሬ ዞን የሳርማሌ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዳኝ አዱላ እንደ ገለጹት፤ ካሳቫ በወረዳቸው ከደጋማው ክፍል በስተቀር በሁሉም አካባቢዎች የሚመረት፣ በሽታ እና የዝናብ እጥረትን የሚቋቋም የሰብል አይነት በመሆኑ የአርሶ አደሩን የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥም ባሻገር ከቡና ቀጥሎ የገቢ ምንጭ ነው።
በአሁኑ ወቅት ከ640 ሄክታር በላይ መሬት በካሳቫ መሸፈኑን የተናገሩት ኃላፊው፤ ከዚህም 163 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት እንደ ሚጠበቅ ነው የገለጹት።
አክለውም ካሳቫ በባህርይው የመሬት ለምነትን የሚጠብቅ በመሆኑ የምርቱ መጠንም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንደሚሄድ አቶ አዳኝ አስረድተዋል።
በወረዳው የጉሙሬ ቀበሌ ግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አንድነት አበራ በበኩላቸው፤ ካሳቫ ተገቢ እንክብካቤ ከተደረገለት ከጥቂት ማሳ ብዙ ምርት እንደሚሰጥ ተናግረዋል።
ካነጋገርናቸው አርሶ አደሮች አቶ አዱኛ አሰፋ እና አቶ አስረስ አላጌ ካሳቫን ከዚህ ቀደም ለቤት ፍጆታ ብቻ ይጠቀሙ እንደነበር ገልጸው፤ በአሁኑ ወቅት የገበያው ተፈላጊነት በመጨመሩና አጠቃቀሙም በመሻሻሉ በስፋት በማምረት ገቢያቸውን እያሳደጉ እንደሚገኙ ተናግረዋል
ዘጋቢ፡ ምርጫ መላኩ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
ከ640 ሄክታር በላይ መሬት በካሳቫ መሸፈኑን በኮሬ ዞን የሳርማሌ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ

More Stories
በክረምት የታየው የበጎ ተግባር ተሳትፎ በበጋ ወራትም በማስቀጠል ደጋፊ የሚሹ ወገኖችን ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ።
የአካባቢ ብክለትን በመቀነስ ውብና ጽዱ አካባቢ ለመፍጠር የደን ልማትና ጥበቃን ማጠናከር እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ደንና አካባቢ ጥበቃ መምሪያ ገለጸ
ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ