በወልቂጤ ከተማ የመሰቀል ደመራ በዓል በተለያዩ ሀይማኖታዊ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል
በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የመሰቀል ደመራ በዓል በተለያዩ ሀይማኖታዊ ሁነቶች በድምቀት እየተከበረ ነው።
የመስቀል ደመራ በዓል ስነ-ስርአት በመላው ኢትዮጵያውያን ዘንድ በየዓመቱ መስከረም 16 ቀን በተለያዩ ኃይማኖታዊ ስርዓቶች እንደሚከበር ይታወቃል።
በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በየዓመቱ በአደባባይ ከምታከብራቸውና በአለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያን ከሚያስተዋዉቁ ሀይማኖታዊ ክብረ በዓላት መካከል የመስቀል ደመራ በዓል አንዱ ነው፡፡
በበዓሉ ላይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የጉራጌ ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ መጋቢ ጥበበ ታምሩ፣ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድርን ጨምሮ ሌሎችም የመንግሥት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና የእምነቱ ተከታዮች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡ ጅላሉ ፈድሉ – ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
በታርጫ ከተማ የደመራ በዓል በድምቀት እየተከበረ ይገኛል
በኮንታ ዞን የደመራ በዓል በተለያዩ ሀይማኖታዊ ክዋኔዎች በመከበር ላይ ይገኛል
የመስቀል ደመራ በዓል በወላይታ ሶዶ ከተማ ሀይማኖታዊ ሥራዓቱን ጠብቆ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል