ህብረተሰቡን ያሳተፉ ወቅታዊ፣ ሚዛናዊ እና ተዓማኒነት ያላቸው መረጃዎችን ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አሳሰበ
የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የቦንጋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ባለፉት ጊዜያት ያከናወናቸውን ተግባራት ተገምግመዋል።
በግምገማ መድረኩ ላይ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ኃላፊ መስፍን ወዳጆ(ዶ/ር)፣ ህብረተሰቡን ባሳተፉ መልኩ ወቅታዊ፣ ሚዛናዊ እና ተዓማኒነት ያላቸው መረጃዎችን ተደራሽ ማድረግ ወሳኝ እንደሆነ ገልጸዋል።
ሚዲያው ከክልላዊና ሀገራዊ የትኩረት አቅጣጫዎች አንጻር ዘመኑን የዋጁ መረጃዎችን በማሰራጨት የአመለካከት ችግሮችን መቅረፍ እንደሚገባው አሳስበዋል።
በመረጃ የዳበረ ዜጋ በመፍጠር ለሀገረ መንግስት ግንባታ ጉልህ አስተዋፅኦ ማበርከት የሚዲያ ተቋማት ዋነኛ ተግባር ሊሆን እንደሚገባ ያስገነዘቡት መስፍን ወዳጆ (ዶ/ር)፤ ተቋሙ የአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ስርፀት ማዕከል በመሆን አሰራሩን ዘመናዊ ማድረግ እንዳለበትም ጠቁመዋል።
የሚዲያ አመራሩና ባለሙያው ተቋሙን በእውቀትና በስነ ምግባር ለመምራት የሚመጥን አስተሣሰብና ክህሎት ሊዳብር ይገባል ብለዋል።
የሚዲያ ባለሙያዎችም እንዲሁ የተቋሙን ነባራዊ ሁኔታ በመረዳት የህብረተሰቡን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ህይወት ለማሻሻል በአዳዲስ አሰራሮች፣ ፈጠራዎችና በሙያዊ ስነ-ምግባር መስራት ይጠበቅባቸዋል ያሉት ደግሞ የካፋ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አዳሙ እሸቱ ናቸው።
የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የቦንጋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ስንታየሁ ሳልልህ የተቋሙን ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት፤ ተቋሙ በ4 የተለያዩ የብሔረሰብ ቋንቋዎች እስከ ታችኛው የህብረተሰብ ክፍል ድረስ በመውረድ ማህበረሰቡን ያማከለ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ሁሉንም የሚዲያ አማራጮች በመጠቀም መረጃን በህዝቡ አፍ መፍቻ ቋንቋ ተደራሽ ለማድረግ የሚደረገው ርብርብ አበረታች መሆኑንም አመልክተዋል።
በሌላ በኩል፤ የሚዲያ ቁሳቁስ ማርጀት፣ የስርጭት ተደራሽነትና የበጀት ውስንነቶች ሊስተካከሉ የሚገባቸው መሆኑን የተቋሙ ሰራተኞች አንስተዋል።
በመጨረሻም የሚስተዋሉ ችግሮችን ደረጃ በደረጃ በመቅረፍና ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር ተቋሙን ወደተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር በትኩረት እንደሚሰራ ተመላክቷል።
ዘጋቢ፡ ትዕግስቱ ጴጥሮስ – ከቦንጋ ጣቢያችን

More Stories
በመስኖ አምርተው የተሻለ ገቢ እያገኙ መሆናቸውን አርሶ አደሮች ተናገሩ
የካፈቾ ዘመን መለወጫ በዓል “ማሽቃሮ” አብሮነትንና ወንድማማችነትን የሚያጎላ ነው – የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ
የኢትዮጵያውያን መገለጫ የሆነውን የመተጋገዝና የመረዳዳት ባህል ይበልጥ በማጎልበት ድጋፍ የሚሹ ወገኖችን ማገዝ እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ አስታወቀ