የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የክልሉ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጳጉሜ 4 “የኅብር ቀን” ለአዲሱ ዓመት ለአቅመ ደካሞች የማዕድ ማጋራት አደረጉ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የክልሉ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጳጉሜ 4 “የኅብር ቀን” ለአዲሱ ዓመት ለአቅመ ደካሞች የማዕድ ማጋራት አደረጉ

ሀዋሳ፡ ጳጉሜ 04/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንዳሻው ሽብሩ፣ የክልሉ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አጉኔ አሾሌን ጨምሮ የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አታ እንዲሁም ሌሎች የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት የጳጉሜ 4 “የኅብር ቀን” እና ለአዲሱ ዓመት የሚሆን ለአቅመ ደካሞች የማዕድ ማጋራት ድጋፎችን አድርገዋል።

የመንግስት የሥራ ኃላፊዎቹ በጂንካ አጠቃላይ ሆስፒል በመገኘት ህሙማንና የአገልግሎት አሰጣጡን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

በሆስፒታሉ ህክምናቸውን ለሚከታተሉ እናቶች ማዕድ የማጋራት ተግባርም አከናውነዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንዳሻው ሽብሩ በዚህን ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፥ በመተባበርና በአንድነት ለውጥ ማምጣት እንደምንችል ማረጋገጥ ተችሏል ብለዋል።

“የኅብር ቀን” ይበልጥ መልካምና በጎ ሥራዎችን አጠናክረን እንድንቀጥል ትልቅ ትርጉም አለው ያሉት አቶ እንዳሻው፤ ቢሮው በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በርካታ ተግባራትን በመፈፀም ውጤት ማስመዝገቡን ገልፀዋል።

ለስኬታማነቱ ለተረባረቡ አካላት የቢሮ ኃላፊው ምስጋና አቅርበዋል።

በክረምት በጎ ፈቃድ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተቋማትና ግለሰቦች የዕውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል።

ዘጋቢ: ተመስገን አበራ – ከጂንካ ጣቢያችን