በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የብሄረሰቦች ምክር ቤት 21ኛው የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓልን አስመልክቶ የተዘጋጀ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የብሄረሰቦች ምክር ቤት 21ኛው የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓልን አስመልክቶ የተዘጋጀ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የብሄረሰቦች ምክር ቤት 21ኛው የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓልን አስመልክቶ የተዘጋጀ የውይይት መድረክ በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

የክልሉ ብሄረሰቦች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ እያሱ ተረፈ በመድረኩ መክፈቻ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ህዳር 29 ቀን 1987 ዓ.ም የኢፌድሪ ሕገ መንግስት የፀደቀበት እና በሀገሪቱ ታሪክ ብዝሃነትን በማስተናገድ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ሕገ መንግሥታዊ ዋስትና የተረጋገጠበት በመሆኑን በየዓመቱ በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር ገልፀዋል፡፡

21ኛው የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓል “በብዝሃነት የደመቀች በምክክር የፀናች ስልጡን ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል የፊታችን ህዳር 29/2019 ዓ.ም በጅማ ከተማ እንደሚከበር አስታውቀዋል።

መድረኩ በክልሉ በየደረጃው የሚከናወን የበዓሉ ቅድመ ዝግጅትና አከባበር ላይ የተቀናጀ አቅጣጫን በመያዝ፣ የባለድርሻ አካላትን ሚና ለማጠናከር እና የጋራ የሥራ እቅድ ላይ ለመወያየት ያለመ ስለመሆኑ አንስተዋል።

በዓሉን አስመልክቶ በየደረጃው የሚከናወኑ ዝግጅቶች አካታች፣ ሕዝባዊ፣ የተቀናጁና የበዓሉን መልዕክት የሚያስተላልፉ እንዲሆኑ ሁሉም አካላት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ አቶ እያሱ ጥሪ አስተላልፈዋል።

በመድረኩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር እና የክልሉ የብሄረሰቦች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ ገመቹ አረቦን ጨምሮ የዞንና የልዩ ወረዳ አፈጉባኤዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ዘጋቢ፡ መሀመድ ሽሁር – ከወልቂጤ ጣቢያችን