ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ጂንካ ከተማ ገቡ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ኣሪ ዞን ጂንካ ከተማ ገብተዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ጂንካ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አፌዶ ወርቁ የተመራ የዞንና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የደቡብ ኦሞ ዞን የአመራሮች ቡድን አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በሚኖራቸው ቆይታም ከመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ከአካባቢ ነዋሪዎች ተወካዮች ጋር ውይይቶችን ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በጉብኝቱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪ አበባየሁ ታደሰ(ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች የክልሉ፣ የዞንና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡ ወንድሜነህ አድማሱ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
የአንድ ማህበረሰብ ቋንቋ ለትውልድ እንዲተላለፍ እና በጽሑፍ እንዲበለጽግ የቋንቋ ሰዋሰው ጥናት ወሳኝ ሚና አለው – የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ባህልና ስፖርት ቢሮ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የብሄረሰቦች ምክር ቤት 21ኛው የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓልን አስመልክቶ የተዘጋጀ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው
የሼሪዓ ፍርድ ቤቶችን አቅም በማጎልበት እና በመደገፍ የፍትህ ስርዓቱ አጋዥ ሆነው እንዲሰሩ የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል – የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት