“ጽናት ለሁለንተናዊ ልዕልና” በሚል መሪ ቃል በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ የጽናት ቀን በተለያዩ መርሃ ግብሮች ተከብሯ

‎የጎፋ ዞን ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር ኃይሉ ወዳጆ ሀገራችን ኢትዮጵያ ችግሮችን በጽናት በመጋፈጥ በርካታ ድሎችን ማስመዝገቧን ተናግረው፤ ሕዝቡ የተጀመሩ ድሎችን ለማስቀጠል በጽናት ከጸጥታ አካላት ጋር መስራት እንዳለበት አሳስበዋል።

‎የሳውላ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ድንበሩ ደርቤ፤ የሀገርን ሠላም ማስጠበቅና ማፅናት የጋራ ትብብር ሰለሚጠይቅ የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን በመቋቋም ሀገር የሚያሻግር ትውልድ ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገለጸዋል

‎ከሠላም ግንባታ ጎን በመሆን የተሰሩና እየተሰሩ ያሉ የልማት ሥራዎች በዘላቂነት እንዲቀጥሉ ሁሉም በጋራ ሊሰራ እንደሚገባም አሳስበዋል።

‎አስተያየታቸውን ያጋሩን የከተማዋ ነዋሪዎች፤ አባቶቻችን ትላንት የአድዋን ድል እንዳስመዘገቡት ሁሉ ዛሬ በአንድነትና በጽናት ተጋምደን ጠንካራ ሀገር በመገንባት የፀናች ኢትዮጵያን ለቀጣዩ ትውልድ ለማሻገር መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

‎ዘጋቢ፡ ስንታየሁ ሙላቱ – ከሳውላ ጣቢያችን