የልማት መጓተትን ለማስቀረትና ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በህብረት ተደጋግፎ መሥራት እንደሚገባ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ጳጉሜ 04/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የልማት መጓተትን ለማስቀረትና ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በህብረት ተደጋግፎ መሥራት እንደሚገባ የባኬቶ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡
የባስኬቶ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የ2018 ዓ.ም ማስፈጸሚያ ማጠቃለያና የ2019 ዓ.ም መሪ ዕቅድ ኦሬንቴሽን መድረክ አካሂዷል።
ብልፅግና ፓርቲ በሪፎርም ሥራዎች በዲሞክራሲ ልምምድ ሂደት የፓለቲካ ተሳትፎን ለማሳደግ ሠፊ ጥረት ማድረጉን የገለጹት የባስኬቶ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ክንፉ ሻቦ ሪፎርሙ ከአስተሳሰብ መግራት እስከ ተቋማት ግንባታ ተግባራትን ያካተተ እንደነበር ገልጸዋል።
የህዝቡን አዳጊ የልማት ፍላጎት ለማሟላት የተፈጥሮ ሀብትን ከሰው ሀይል ጋር አቀናጅቶ መምራት የፓርቲው ትልቁ ራዕይ በመሆኑ ይበልጥ በትኩረት መሥራት ይገባል ብለዋል።
በተለያዩ ዘርፎች ከመደበኛ ሥራዎች ባሻገር የኢኒሼቲቭ ተግባራትን በአግባቡ በመምራት የታሠበውን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማምጣት እንደሚሠራም አረጋግጠዋል።
የዞኑን ሠላምና ጸጥታ ማረጋገጥ የልማት ቁልፍ መሠረት በመሆኑ የህግና ደንብ አስከባሪ አካላትን መደገፍና ማጠናከር ይገባል ብለዋል።
የባስኬቶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢ/ር በዛብህ ገበዬሁ በጉባኤው መግቢያ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ብልጽግና ፓርቲ እንደ ሀገር፣ በክልልና በዞን ደረጃ ሰፋፊ ለውጦችና ትሩፋቶችን ማስመዝገቡን አብራርተዋል።
በባስኬቶ ዞን በጤናው፣ በትምህርት፣ በግብርና እንዲሁም በገጠር ንጹህ የመጠጥ ውሃ ተደራሽነትና በመስኖ አውታሮች ግንባታ የተመዘገቡ ውጤቶችን ለአብነት ጠቅሠዋል።
የባስኬቶ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የ2018 ዓ.ም ማስፈጸሚያ ማጠቃለያና የ2019 ዓ.ም መሪ ዕቅድ በብልጽግና ፓርቲ ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊው አቶ በሀይሉ ባባሮ ቀርቧል።
በተጨማሪም በፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን የተከናወኑ ዝርዝር ተግባራት በኃላፊው አቶ አናጋው ደጀኔ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
በተደረገው ውይይት መነሻም በተነሱ ጉዳዮች ላይ በዞኑ ዋና አስተዳዳሪና በብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊው ምላሽና ማብራሪያ እየተሰጠበት ይገኛል።
ዘጋቢ: አወል ከድር – ከሳውላ ጣቢያችን

More Stories
ከፋፋይ ከሆኑ አጀንዳዎች በመራቅ ህብረታችንን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ
በሀድያ ዞን ጎምቦራ ወረዳ ሀብቾ ከተማ ነዋሪ ለሆኑ አንዲት አቅመ ደካማ እናት የመኖሪያ ቤት ርክክብ ተደረገ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የክልሉ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጳጉሜ 4 “የኅብር ቀን” ለአዲሱ ዓመት ለአቅመ ደካሞች የማዕድ ማጋራት አደረጉ