ማርሊ ሳልሞን የመጀመሪያውን ፕሮፌሽናል ኮንትራት ፈረመ
የአርሰናል አካደሚ ውጤት የሆነው ተከላካዩ ማርሊ ሳልሞን ከሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ጋር የመጀመሪያውን ፕሮፌሽናል ኮንትራት መፈረሙን ክለቡ ይፋ አድርጓል።
ክለቡ የ17ኛ ዓመት የልደት በዓሉን በሚያከብርበት ዕለት የውል ስምምነቱን ይፋ ማድረጉ ለቀኑ ልዩ ድምቀት ሰጥቶታል::
ሳልሞን ስምምነቱን ከፈፀመ በኋላ ለአርሰናል ድህረ ገጽ በሰጠው አስተያየት “ይህ ለእኔ ትልቅ ትርጉም አለው። በርካታ ውጣ ውረዶችና ከፍተኛ ጥረት ያለፈበት መንገድ ነው፤ ውጤቱን በማየቴም እጅግ ኮርቻለሁ” ሲል ተናግሯል።
ተጫዋቹ አክሎም “ይህ ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለቤተሰቦቼም ጭምር ኩራትና ትልቅ ሽልማት ነው። ለእኔ ጊዜያቸውንና ድካማቸውን ስለሰጡ፣ ይህ የእነሱም የጠንካራ ሥራ ውጤት ነውሸ” ብሏል።
ማርሊ ሳልሞኖ በአካደሚው ያሳየውን ፈጣን እድገትና ድንቅ ብቃት ተከትሎ ባለፈው የውድድር ዘመን ለዋናው ቡድን 5 ጨዋታዎችን ማድረግ ችሏል።
ከነዚህ ጨዋታዎች መካከል በትልቁ የግሎቦች ውድድር የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ከክሉብ ብሩጅ ጋር በነበረው ጨዋታ ተቀይሮ ገብቶ ያደረገው ተሳትፎ ይጠቀሳል።
ዘጋቢ ፡ ሙሉቀን ባሳ
ማርሊ ሳልሞን የመጀመሪያውን ፕሮፌሽናል ኮንትራት ፈረመ

More Stories
ሊቨርፑል ብራድሌይ ባርኮላን ለማስፈረም ከፒኤስጂ ጋር ከስምምነት ደረሰ
የአርሰናሉ ኮከብ አዲስ ተስፋና ተነሳሽነት
ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝ ወደ ቼልሲ ለመዛወር ራሱን በእጩነት አቀረበ