ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በተገኙበት በጉራጌ ዞን ጉንችሬ ከተማ አስተዳደር ከ114 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ የቅድመ መደበኛና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲሁም የጤና ጣቢያ የምረቃ ስነ-ስርአት እየተካሄደ ይገኛል
ሀዋሳ፡ ነሐሴ 23/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በተገኙበት በጉራጌ ዞን ጉንችሬ ከተማ አስተዳደር ከ114 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ የጉንችሬ ብራይት ቅድመ መደበኛና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲሁም የጉንችሬ ከተማ ጤና ጣቢያ የምረቃ ስነ-ስርአት እየተካሄደ ይገኛል።
በምረቃ ስነ-ስርአቱ ላይ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ፣ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል እርስቱ ይርዳውና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው የክልልና የዞን አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።
ዘጋቢ፡ ፉአድ አብደላ – ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
የገቢ መሠረቶችን አሟጦ በመጠቀምና በመሠብሰብ የዞኑን የገቢ አቅም ይበልጥ ማሳደግ እንደሚገባ የጋሞ ዞን አስተዳደር አስታወቀ
ኤንዞ ፌርናንዴዝ ከማንችስተር ሲቲ ጋር በግል ጉዳዮች ከስምምነት ላይ ደረሰ!
የዳውሮ ብሔር ዘመን መለወጫ “ቶክ በኣ” በዓል ባህልን ጠብቆ ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማሸጋገር እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ