ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝ ወደ ቼልሲ ለመዛወር ራሱን በእጩነት አቀረበ

ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝ ወደ ቼልሲ ለመዛወር ራሱን በእጩነት አቀረበ

የአስቶን ቪላ እና የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን የግብ ጠባቂ የሆነው ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝ ራሱን በእጩነት ለቼልሲ ማቅረቡ የተሰማ ሲሆን፣ የምዕራብ ለንደኑ ክለብም የ33 ዓመቱን ግብ ጠባቂ ለማስፈረም እየመከረበት እንደሚገኝ ተዘግቧል።

ቼልሲ አዲሱን የውድድር ዓመት ፉልሃምን 3 ለ 2 በማሸነፍ ቢጀምርም፣ በጨዋታው ላይ ሁለት ስህተቶችን የሰራው ሮበርት ሳንቼዝ አሁንም የቋሚነት ቦታው አስተማማኝ አለመሆኑን አሳይቷል።

የዉሰት ቆይታዉን አጠናቆ ከስትራዝቡርግ የተመለሰው የ21 ዓመቱ ማይክ ፔንደርስ በተጠባባቂ ወንበር ላይ ቢቀመጥም፣ ክለቡ ልምድ ያለው የመጀመሪያ ግብ ጠባቂ ይፈልጋል።

ማርቲኔዝ በዚህ ክረምት ክለቡን ለመልቀቅ ጥረት ሲያደርግ የመጀመሪያው አይደለም። ቀደም ሲል ከጁቬንቱስ ጋር ንግግሮች ቢደረጉም ዝውውሩ ሳይሳካ ቀርቷል።

አስቶን ቪላ ዛዮን ሱዙኪን ከፓርማ ያስፈረመ ሲሆን፣ በፕሪሚየር ሊጉ የመክፈቻ ጨዋታ በብራይተን 4ለ0 በተሸነፈበት ጨዋታ ላይ ማርኮ ቢዞት በቋሚነት ተሰልፏል።

ማርቲኔዝ እ.ኤ.አ. በ2020 ከአርሰናል ከተቀላቀለ ወዲህ ለቪላ 256 ጨዋታዎችን አድርጓል። ባለፈው የውድድር ዘመን ቡድኑ 4ኛ ደረጃን ይዞ እንዲያጠናቅቅ፣ የዩሮፓ ሊግ ዋንጫን እንዲያነሳና ወደ ቻምፒየንስ ሊግ እንዲመለስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷል።

በተጨማሪም በክረምቱ የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ባደረገው ጉዞ በሁሉም 8 ጨዋታዎች በቋሚነት ተሰልፎ ተጫውቷል።

አስቶን ቪላ በዚህ ክረምት እንደ ሞርጋን ሮጀርስ፣ ዩሪ ቲሌማንስ እና ኤዝሪ ኮንሳ ያሉ ቁልፍ ተጫዋቾችን በመሸጥ በስብስቡ ላይ ትልቅ ለውጥ እያደረገ ባለበት በዚህ ወቅት፣ የማርቲኔዝ ወደ ለንደን ማምራት ቀጣዩ ትልቅ የክረምቱ ዝውውር ሊሆን ይችላል።

ዘጋቢ ፡ ሙሉቀን ባሳ