ሊቨርፑል ብራድሌይ ባርኮላን ለማስፈረም ከፒኤስጂ ጋር ከስምምነት ደረሰ
የእንግሊዙ ክለብ ሊቨርፑል የፓሪስ ሴንት ዠርሜኑን ፈጣን አጥቂ ብራድሌይ ባርኮላን በ120 ሚሊዮን ፓውንድ አጠቃላይ የዝውውር ሂሳብ ለማስፈረም ከፈረንሳዩ ክለብ ጋር ከመሰረታዊ ስምምነት ላይ መድረሱ ተገልጿል።
ሁለቱ ክለቦች ከ100 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ በቅድሚያ የሚከፈል እንዲሁም ቀሪው በቦነስ መልክ የሚካተትበትን የ120 ሚሊዮን ፓውንድ ጥቅል ሂሳብ ዙሪያ መስማማታቸውን ዘ አትሌቲክ አስነብቧል።
ምንም እንኳን የውል ስምምነቶች እስካሁን ባይፈረሙም በዛሬው ዕለት የዝውውሩን የመጨረሻ ዝርዝሮች የማጠናቀቅ ስራ እየተሰራ ይገኛል።
የ23 ዓመቱ የፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን አጥቂ በዚህ ክረምት የሊቨርፑል ዋና የዝውውር ኢላማ የነበረ ሲሆን፡ ወደ አንፊልድ ለመዛወር ሙሉ ፍላጎት እንዳለው አሳይቷል።
በፒኤስጂ የሁለት ዓመት ውል ቢቀረውም አዲስ ውል ላለመፈረም በመወሰኑ፡ ክለቡ በቅርቡ ከሬን ጋር 2 ለ 2 በተለያየበት የሊግ መክፈቻ ጨዋታ ላይ ከስብስቡ ውጪ መደረጉ ይታወቃል።
ዘጋቢ ፡ ሙሉቀን ባሳ
ሊቨርፑል ብራድሌይ ባርኮላን ለማስፈረም ከፒኤስጂ ጋር ከስምምነት ደረሰ

More Stories
ማንችስተር ዩናይትድ ከሊድስ ዩናይትድ ጋር ሲፋለም አርሰናል ከሜዳው ውጪ ወሳኝ ጨዋታ ይጠብቀዋል
የቀድሞው የማንችስተር ሲቲ እና የሌስተር ሲቲ ኮከብ ሪያድ ማህሬዝ አዲስ ክለብ አግኝቷል።
አርሰናል ሰራተኞቹን ከስራ ሊያሰናብት ነው