ካርሎስ ባሌባ ለማንቼስተር ዩናይትድ ፊርማውን አኖረ
ማንቼስተር ዩናይትድ የብራይተኑን አማካኝ ካርሎስ ባሌባን ለማስፈረም የሚያስችለውን ሙሉ ስምምነት ላይ መድረሱ ተረጋግጧል።
ሁለቱ ክለቦች ስምምነቱን የሚያጠናቅቁ ህጋዊ ሰነዶችን የተለዋወጡ ሲሆን፣ ዝውውሩን ይፋ ለማድረግ ጥቂት ዝርዝሮች ብቻ እንደቀሩት ተዘግቧል።
ዩናይትድ 65 ሚሊዮን ፓውንድ ቋሚ ክፍያ እና ተጨማሪ 5 ሚሊዮን ፓውንድ የሚያካትት ጠቅላላ 70 ሚሊዮን ፓውንድ ጥቅል ሒሳብ ለብራይተን እንደሚከፍል ተገልጿል።
ተጫዋቹ እ.ኤ.አ እስከ ሰኔ 2031 የሚያቆየውን ባለ 5 ዓመት ውል የተፈራረመ ሲሆን፣ የውል ዘመኑን ለተጨማሪ አንድ ዓመት ማራዘም የሚያስችል አንቀፅ በውሉ ላይ ተካቷል።
ካርሎስ ባሌባ የመጀመሪያውን ዙር የሕክምና ምርመራ በስኬት አጠናቋል።
የ 22 ዓመቱ ካሜሩናዊ አማካኝ በብራይተን ቤት ባሳየው ድንቅ ብቃት ፣ ማንቼስተር ዩናይትድ የመሃል ሜዳ ክፍሉን ለማጠናከር ባደረገው ጥረት ተጫዋቹን የግሉ ማድረግ ችሏል።
ዝውውሩ በቅርብ ሰዓታት ውስጥ በዩናይትድ በኩል በይፋ እንደሚደረግ ይጠበቃል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
አርሰናል ከ ላምፓርዱ ኮቨንተሪ ሲቲ
አርሰናል ኤዝሪ ኮንሳን በ55 ሚሊዮን ፓውንድ የዝውውር ሂሳብ አስፈረመ
ቶተንሃም ሳቪንሆን በ85 ሚሊዮን ፓውንድ ለማስፈረም ከስምምነት ደረሰ