የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመገንባት የስራ ዕድል ፈጠራ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ነሐሴ 20/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመገንባት የስራ ዕድል ፈጠራ ወሳኝ ነው ሲል የይርጋጨፌ ከተማ አስተዳደር ገለጸ፡፡
በጌዴኦ ዞን የይርጋጨፌ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ፅህፈት ቤት የ2018 አፈፃፀምና በ2019 በጀት ዓመት እቅድ ዙሪያ የሚመክር የስራ ዕድል ፈጠራ ምክርቤት ጉባኤ እያካሄደ ነው።
በመርሀ ግብሩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የይርጋጨፌ ከተማ ከንቲባ አቶ ብዙአየሁ ታደሰ፥ የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመገንባት የስራ ዕድል ፈጠራ ወሳኝ በመሆኑ በትኩረት ሊተገበር ይገባል ብለዋል።
ዜጎች እንደ ከተማ ያለውን ዕድልና ፀጋዎችን በመጠቀም በስራ ዕድል ፈጠራ ላይ በመሰማራት ኢኮኖሚያቸውን በማሳደግ ተጠቃሚ መሆን አለባቸው በማለት ከንቲባው ተናግረዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ ከወትሮ በተለየ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ላይ ወጣቶች ህይወታቸውንና ኑሮአቸውን እንዲያሻሽሉ በማድረግ ረገድ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን አንስተዋል።
በተለይም ተግባሩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትና ተቋማት ጋር በመቀናጀት በብድር አመላለስ፣ በቋሚ የስራ ዕድል ፈጠራና ተከታታይ የክህሎት የአቅም ግንባታ መሙያ ስልጠና በመስጠት የተሻለ ውጤት መመዝገብ መቻሉን ከንቲባው አብራርተዋል።
በቀጣይም የዘርፉን ተግባር ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ በወጣቶች አመለካከትና አስተሳሰብ በቁጠባ ብሎም የተሻለ ምርት በጥራት ከማቅረብና ተወዳዳሪ ከመሆን አንፃር ውስንነት ያለበትና በቀጣይ በትኩረት የሚተገበር መሆኑን ከንቲባው አመላክተዋል ።
የይርጋጨፌ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የሥራና ክህሎት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ዮሴፍ አየለ እንደ ሀገር የተረጋጋ ኢኮኖሚና ዘላቂ ሠላም እንዲሰፍን የስራ ዕድል ፈጠራ ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል።
አክለውም አቶ ዮሴፍ የዘርፉን ተግባር ውጤታማ ለማድረግ የቅርብ ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ በመሆኑ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ አንስተው በቀጣይ ተግባሩን በቴክኖሎጂ የታገዘ የምዝገባ ስራዎች ስለሚከናወኑ ሁላችንም የድርሻችንን መወጣት ይጠበቅብናል ብለዋል።
በምክክሩ የከተማ አመራሮች የሚመለከታቸው አካላት እንዲሁም ግንባር ቀደም የኢንተርፕራይዞች አባላት ታድመዋል።
ዘጋቢ ፡ ፅጌ ደምሴ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን

More Stories
የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ተቋማት በመንግስት እና በህዝብ መካከል የመረጃ ግልፀኝነት በመፍጠር የልማትና መልካም አስተዳደር ተግባራት በውጤታማነት እንዲፈፀሙ ጉልህ ሚና በመጫወት ላይ እንደሚገኙ ተገለፀ
የአርባምንጭ ከተማ ሰላማዊና በተፈጥሮ ፀጋ የበለፀገለች መሆኗ ለቱሪዝም ዘርፍ ተመራጭ ያደርጋታል – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ
የሀለባ ዞን ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ከ3 ቢልዮን 293 ሚልዮን ብር ባለይ በጀት አጸደቀ