የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ተቋማት በመንግስት እና በህዝብ መካከል የመረጃ ግልፀኝነት በመፍጠር የልማትና መልካም አስተዳደር ተግባራት በውጤታማነት እንዲፈፀሙ ጉልህ ሚና በመጫወት ላይ እንደሚገኙ ተገለፀ
የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ የ2018 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማና የ2019 በጀት አመት ጠቋሚ እቅድ ማስተዋወቂያ የንቅናቄ መድረክ እያካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የዞኑ ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ፤ ሚዲያ በዞኑ እየተሰሩ ባሉ የልማትና የመልካም እስተዳደር ስራዎች ላይ ህዝቡንና መንግስትን የሚያገናኝ ድልድይ ነው ሲሉ ገልፀዋል።
በዞኑ የሚዲያ ተግባር ጥራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ያወሱት አቶ አበራ፤ በዚህም የማህበረሰቡ ተሳትፎ የሚበረታታ ነው ብለዋል።
ሚዲያ ለልማትም ለጥፋትም ያለው ጉልበት ሀያል ነው ያሉት አቶ አበራ፤ የተጀመረውን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ ልማታዊ በሆነ እሳቤ ላይ የተመሰረት ለህዝብ ትክክለኛ መረጃ በጥራትና በፍጥነት ለማስተላለፍ በትኩረት መስራት ይጠበቃል ሲሉም አሳስበዋል።
የዞኑ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ሸምሱ አማን፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ በ2030 ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እያከናወነች እንደምትገኝ ገልፀው ተቋማቸውም በዚህ የዲጂታል ዘመን ጥራት ያለው መረጃን ለማሰራጨት በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
በተለይም በመንግስት እና በህዝብ መካከል እምነትን በመገንባትና ተቋማዊ አስተዳደርን በማራመድ በግልፀኝነት እና በተጠያቂነት ላይ የተመሰረት መረጃ እያሰራጨ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል አቶ ሸምሱ።
በመድረኩ የጉራጌ ዞን ምክር ቤት የማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ጥሩነሽ ምኑታ፣ በደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የወልቂጤ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ፍቃዱ ዘለቀ፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር የኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የማኔጅመት አባላት እና ሌሎችም ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡ እርካብነሽ ወ/ማርቆስ – ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ የንብረት ግዥን አስመልክቶ ከክልሉ መንግስት የተሰጠ መግለጫ
የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመገንባት የስራ ዕድል ፈጠራ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ
በተጠናቀቀው በጀት አመት እንደሀገርም ሆነ ልዩ ወረዳ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በመቅረፍ ስኬታማ ተግባራት መከናወናቸውን በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቀቤና ልዩ ወረዳ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገለፀ