አርሰናል ኤዝሪ ኮንሳን በ55 ሚሊዮን ፓውንድ የዝውውር ሂሳብ አስፈረመ

አርሰናል ኤዝሪ ኮንሳን በ55 ሚሊዮን ፓውንድ የዝውውር ሂሳብ አስፈረመ

የፕሪሚየር ሊጉ አሸናፊ አርሰናል እንግሊዛዊውን የተከላካይ መስመር ተጫዋች ኤዝሪ ኮንሳን ከአስቶንቪላ በቋሚ ዝውውር ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል።

ዝውውሩ 51 ሚሊዮን ፓውንድ ቀጥተኛ ክፍያ እና ተጨማሪ 4 ሚሊዮን ፓውንድ ያካተተ መሆኑን ዘ አትሌቲክ አስነብቧል።

የ 28 ዓመቱ ኤዝሪ ኮንሳን በሰሜን ለንደኑ ክለብ የሕክምና ምርመራውን ካጠናቀቀ በኋላ፣ ተጨማሪ የአንድ ዓመት ማራዘሚያ አማራጭ ያለው የ4 ዓመታት ኮንትራት መፈራረሙ ተገልጿል።

ይህ ዝውውር አርሰናል በክረምቱ የዝውውር መስኮት ያደረገውን ጠንካራ እንቅስቃሴ የሚያሳይ ሲሆን፣ ክለቡ ቀደም ብሎ ክሪስቶስ ዞሊስን ከክለብ ብሩጅ፣ ብሩኖ ጊማራኤሽን ከኒውካስል ዩናይትድ እና ግብ ጠባቂው ኢላን መሴሊየርን ከሊድስ ዩናይትድ ማስፈረሙ ይታወሳል።

በሌላ በኩል አስቶንቪላ በዚሁ የዝውውር መስኮት በርካታ ዋና ተጫዋቾቹን ያጣ ሲሆን ሞርጋን ሮጀርስ ወደ ቼልሲ፣ ሉካስ ዲግኔ ወደ ፒኤስጂ እንዲሁም ዩሪ ቲሌማንስ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ ማምራታቸው አይዘነጋም።

አርሰናል የ2026/27 የፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታውን በዛሬው ዕለት በኤሚሬትስ ስታዲየም ከአዲሱ አዳጊ ኮቬንትሪ ሲቲ ጋር የሚያደርግ ሲሆን፣ አስቶንቪላ ደግሞ እሁድ ዕለት በአመክስ ስታዲየም ከብራይተን ጋር የውድድር ዓመቱን የመጀመሪያ ጨዋታውን ያከናውናል።

ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ