የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ የእናቶች ጤናና የሥርዓተ-ምግብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የ2018 ባጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም መድረክ በሆሳዕና ከተማ እያካሄደ ይገኛል
በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮው ምክትል ኃላፊና የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሸናፊ ጴጥሮስ፥ በ2018 ባጀት ዓመት የእናቶች፣ የህፃናትና የጨቅላ ህፃናት ጤናና የስርዓተ ምግብ አገልግሎት የተሻለ አፈፃፀም መመዝገቡን ጠቁመዋል::
በዚህም ካላፈው ባጀት ዓመት የእናቶች እና የህፃናት የሞት ምጣኔን በ3 ነጥብ 9 በመቶ በማሳደግ የተሻለ አፈፃፀም ተመዝግቧል ብለዋል::
የህብረተሰቡ የጎላ ተሣትፎ ለዘርፉ ውጤታማነት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ስለማበርከቱም አቶ አሸናፊ ገልፀዋል::
በመድረኩ የክልሉ፣ የዞን እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል::
ዘጋቢ: አብዱልሰመድ አወል – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
የአፈር ጤናን በመጠበቅና ለምነትን በማሻሻል የአርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢኒስቲትዩት የወራቤ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ።
የሕዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ በትኩረት ይሠራል – የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)
ጥራቱ የተጠበቀ ከ500 ቶን በላይ እሸት ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ