የ2018 ዓ.ም ክልላዊ የ8ኛ እና 6ኛ ክፍል ፈተና ውጤት መነሻ ያሉባቸውን ክፍተት በአዲሱ 2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለመሻገር በልዩ ቁርጠኝነት እንደሚሠሩ የየዞኑ የትምህርት አመራሮች ገለፁ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ሐምሌ 28/2018 ዓ.ም የ8ኛና የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ማድረጉ የሚታወቅ ሲሆን ከውጤቱ መነሻ ገና ብዙ ሥራን እንደሚጠይቅ ነው ውጤቱ በተገለጸበት ዕለት በክልሉ ካሉ ዞኖች የትምህርት ዘርፉን የሚመሩ አካላት ተገኝተው ይህንን የገለፁት።
የተሻለ አፈፃፀም ያስመዘገቡ መዋቅሮች እንዳሉ ሁሉ ሰፊ ክፍተት ያለባቸው መኖራቸውን መገንዘባቸውን የጠቀሱት አመራሮቹ፤ የተማሪዎች ውጤት በሁሉም መዋቅር ወጥነት ባለው መልኩ እንዲሆን ልዩ ትኩረትና ቁርጠኝነት ይሻል ብለዋል።
ለዝቅተኛ ውጤት መነሻ የሆኑ ምክንያቶችን ለይተው መፍትሄው ላይ እንደሚሠሩም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ እንዲሁም የመማር ማስተማሩን ስራ በአግባቡ የመሩ መዋቅሮች በዚሁ ልክ ውጤት መመዝገቡን ገልፀው፤ በአንፃሩ በተለያየ መልክ የሚገለፅ ችግሮች ባሉባቸው ደግሞ ክፍተት ተስተውሏል ሲሉም ተናግረዋል።
ታዲያ ይህንን የውጤት ወጥነት የሚጎለውን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ከትምህርት አመራር፣ መምህራን፣ ተማሪዎችና አጠቃላይ ህዝብ ለነገ የማይባል የቤት ሥራ በመኖሩ ሁላችንም በጋራ ቅንጅት በትምህርት ልማት ላይ ልንዘምት ይገባናል ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።
አሁን ወቅቱ የ2019 የትምህርት ዘመን ምዝገባ የሚካሄድበት በመሆኑ ሁሉም የክልሉ ህዝብ ተማሪዎችን በጊዜ በማስመዝገብ የመማር ማስተማሩ ሂደት በክልሉ ትምህርት ቢሮ በኩል በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ እንዲጀመር ሁላችንም ሃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባናል ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ: ተመስገን አበራ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
የመረጃ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የተቋሙ ሰራተኞች በአደረጉት ጥረት የተሻለ ውጤት መመዝገቡን በደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የሚዛን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ
ኒውካስል ዩናይትድ ብሩኖ ጊማሬሽን በ75 ሚሊዮን ፓውንድ ለአርሰናል ለመሸጥ ተስማማ
በሸካ ዞን የኪ ወረዳ በቆ ቀበሌ በ36 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የገጠር ሞዴል መንደር ተመረቀ