ዛሬ የምንተክለው እያንዳንዱ ችግኝ የነገዋን አረንጓዴ፣ ለምለም፣ የተደላደለችና የበለጸገች ከምባታን የመገንቢያ ጠንካራ መሰረት የምንጥልበት ነው አሉ የከምባታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አረጋ እሸቱ

ዛሬ የምንተክለው እያንዳንዱ ችግኝ የነገዋን አረንጓዴ፣ ለምለም፣ የተደላደለችና የበለጸገች ከምባታን የመገንቢያ ጠንካራ መሰረት የምንጥልበት ነው አሉ የከምባታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አረጋ እሸቱ

በከንባታ ዞን ቀዲዳ ጋሜላ ወረዳ ደጋ ቀዲዳ ቀበሌ ሀሮ ተከላ ሳይት የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላን በይፋ ያስጀመሩት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አረጋ ተሾመ በዚሁ ታላቅ ቀን፣ በክልሉ 10 ማሊዮን በዞን ደግሞ በአንድ ጀምበር 1.6 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል በጋራ በመሰብሰባችን ከፍ ያለ ኩራትና የላቀ ደስታ ተሰምቶኛል ብለዋል።

የዛሬው ዕለት እንደ ዋዛ የችግኝ ተከላ የምናካሂድበት ቀን አይደለም ያሉት አስተዳዳሪው ዛሬ የምንተክለው እያንዳንዱ ችግኝ የነገዋን አረንጓዴ፣ ለምለም፣ የተደላደለችና የበለጸገች ከምባታን የመገንቢያ ጠንካራ መሰረት የምንጥልበት ነው በለዋል።

“ዛሬ የምንተክለው ችግኝ የአፈር መሸርሸርን ለመግታት፣ የምንጮቻችንን ውሃ ለማደስ፣ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም እና ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች ምድር ለማስረከብ የምናደርገው የተፈጥሮ ጥበቃ ተጋድሎ ዋነኛ አካል ነው” ሲሉም አስተዳዳሪው ገልፀዋል።

አቶ አረጋ አክለውም የከምባታ ህዝብ በታሪኩ በተፈጥሮ ጥበቃው፣ በስራ ወዳድነቱና አካባቢውን በጥንቃቄ በመንከባከብ ረገድ ረጅም ዘመናትን የተሻገረ የባህልና የባለቤትነት ዕውቀት እንዳለው ሁላችንም የምናውቀው ሃቅ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

“ዛሬም ይህንን ታላቅ ሀገራዊ ጥሪ ተቀብለን፣ በአንድ ጀምበር 1.6 ሚሊዮን ችግኞችን በዞናችን በገጠር ቀበሌዎች፣ በተራቆቱ መሬቶችና በየደጃፋችን ለመትከል በቁርጠኝነት ተነስተናል” ሲሉ ገልጸዋል።

ይህ ታላቅ እቅድ በተሳካ ሁኔታ ከመሬት እንዲወርድ ካለፉት ወራት ጀምሮ ጉድጓድ ዝግጅት፣ ጥራት ያላቸው ችግኞችን በማዘጋጀትና ህዝባችንን በማስተባበር ሌት ተቀን የደከማችሁትን አመራሮችን የግብርና ባለሙያዎቻችንን፣ ወጣቶችን፣ ሴቶችን፣ የጸጥታ አካላትን እና በዞኑ አስተዳደር እና በራሴ ስም ከልብ ላመሰግን እወዳለሁም ብለዋል።

በመርሀ ግብሩ ላይ የከምባታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አረጋ እሸቱ፣ የከምባታ ዞን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ አስካለ ሰሶ፣ የከምባታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና የዞኑ ዋና የመንግሥት ተጠሪ አቶ ተክሌ ስዩምን ጨምሮ የዞንና የወረዳ አመራሮች፣ የመንግሥት ሠራተኞችና የአካባቢው ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።

ዘጋቢ: ምስጋና ኤልያስ