እንደ ሀገር ”በጋራ ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሃ-ግብር በሸካ ዞን በማሻ ማረሚያ ተቋም ተካሄደ
ሀዋሳ፡ ሐምሌ 27/2018ዓ.ም (ደሬቴድ)እንደሀገር ”በጋራ ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሃ-ግብር በሸካ ዞን በማሻ ማረሚያ ተቋም ተካሂዷል።
በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል አዲስ ታሪክ የሚጻፍበት ሀገራዊ መርሃ-ግብር አካል የሆነው በክልሉ 25 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ ስነ-ስርዓትን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ህይወት አሰግድ በሸካ ዞን ማሻ ከተማ አስጀምረዋል።
ኃላፊዋ በወቅቱ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢኒሼቲቭ የሆነውን የአርንጓዴ አሻራ መረሃ-ግብር ሀገርን የማጽናትና የማሻገር በመሆኑ በዛሬው ዕለት በዩኒስኮ የተመዘገበ ጥብቅ ደን ያለበት ሸካ ዞን ማሻ ከተማ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸውን ችግኝ ተክለናል ብለዋል።
የቢሮ ኃላፊዋ መርሃ-ግብሩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፤ መላው ኢትዮጵያውያን ምድርን ለማዳን እና እንደተለመደው ታሪክ ለመሥራት በአንድነት መነሣታቸውን ገልጸዋል።
መረሃ-ግብሩ ሀገሪቱ በውስጥ ጉዳይዋ እየመከረችና እያጸናች ባለችበት ወቅት መሆኑን የተናገሩት የቢሮ ኃላፊዋ የሚተከሉት ችግኞች የአየር ንብረት ሚዛንን ከመጠበቅ ባሻገር ለህዝባችን ኢኮኖሚ ፋይዳ ያላቸው በመሆኑ የመንከባከብና የጽድቀት መጠኑን ከፍ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
የአረንጓዴ አሻራ መረሃ-ግብርን በማረሚያ ተቋም ያስጀመሩት ቢሮ ኃላፊዋ ከዚህ በፊት የተተከሉት ችግኞች የጽድቀት መጠናቸው ከፍተኛ መሆኑን መመልከታቸውን ተናግረዋል።
በመደመር መርህ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል በአንድነት ወጥቶ ለቀጣዩ ትውልድ የሚተላለፍ አሻራውን እንዲያሳርፍና “ኑ ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ሐሳብ ደማቅ ተሳትፎ እንዲያደርግ ወ/ሮ ህይወት ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
እንደሀገር በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን የሚተከል ሲሆን፤ እንደ ክልል 25 ሚሊዮን የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ የሚከናወን መሆኑ ይታወቃል።
ዘጋቢ: ካሳሁን ደንበሎ – ከማሻ ጣቢያችን

More Stories
ችግኝ መትከል ጥሪት ለትውልድ የማስቀመጥ ተግባር በመሆኑ ለተግባራዊነቱ በቅንጅት መረባረብ እንደሚገባ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ሙስጠፋ ኢሳ ገለፁ።
በሀዋሳ ከተማም ከ220 ሺህ በላይ ችግኞችን በ8ቱም ክፍለ ከተሞች ”ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል”እየተከለች ነው።
በኣሪ ዞን በባካ ዳዉላ ኣሪ ወረዳ “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል የአንድ ጀምበር አረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር እየተካሄደ ይገኛል