ችግኝ መትከል ጥሪት ለትውልድ የማስቀመጥ ተግባር በመሆኑ ለተግባራዊነቱ በቅንጅት መረባረብ እንደሚገባ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ሙስጠፋ ኢሳ ገለፁ።
ሀገራዊ የ800 ሚሊየን ችግኝ በአንድ ጀምበር ተከላ መርሀ ግብር በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ በያስሁራና ዋርቢያ ቀበሌ የዳምሳር ተፋሰስ በመከናወን ላይ ይገኛል።
የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ሙስጠፋ ኢሳ በመርሃ ግብሩ ላይ እንዳሉት “ችግኝ መትከል ጥሪት ለትውልድ የማስቀመጥ ተግባር በመሆኑ ለተግባራዊነቱ በቅንጅት መረባረብ ይገባል” ብለዋል።
በመርሃ ግብሩ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ሙስጠፋ ኢሳ፣ የጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅሕፈት ቤት ሀላፊ አቶ ናስር ሀሰንን ጨምሮ ሌሎች የክልል፣ የዞን፣ የወረዳና ከተማ አስተዳደር የስራ ሀላፊዎች እና የቀበሌው የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳትፈውበታል።
ዘጋቢ፣ አማረ መንገሻ – ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
መሳላ የሕዝቦችን ትስስር፣ አንድነትና መከባበርን የሚያጎለብት ታላቅ በዓል ነው – የተለያዩ ብሔር ብሔረሰብ ተወካዮች
የሀድያ ብሔር ዘመን መለወጫ “ያሆዴ” በዓል ከብሔሩ ዘመን መለወጫነት ባሻገር የሚያበረክተው ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ የጎላ ነው – የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቴዎስ አኒዮ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የ”ያሆዴ” በዓልን ስናከብር ስለ ሀገራችን ልማትና ስለ ህዝባችን አብሮነት የበለጠ የምንተጋበት ወቅት ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል