በሀዋሳ ከተማም ከ220 ሺህ በላይ ችግኞችን በ8ቱም ክፍለ ከተሞች ”ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል”እየተከለች ነው።
የአየር ንብረት ለውጥ፣ የምግብ ዋስትናና የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ የዓለም ትልቅ ፈተናዎች በሆኑበት ወቅት፣ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ታላቅ ግብ ይዛ ወደ ተግባር ገብታለች።
የዚህ ሀገራዊ ዘመቻ አካል የሆነችው ሀዋሳ ከተማም በ8ቱም ክፍለ ከተሞቿ ከ220 ሺህ በላይ ችግኞችን በመትከል የሀዋሳ ሐይቅን ለመጠበቅ፣አረንጓዴ ሽፋኗን ለማሳደግና የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት ያላትን ቁርጠኝነት እያረጋገጠች ነው።
በመርሃ ግብሩ የተገኙት የኢፌዴሪ የአደጋና ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም፣ የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም የሚቻለው በንግግር ሳይሆን በተግባር መሆኑን ገልጸው፣”ችግኝ መትከል ተስፋን መትከል ነው፤ ዛሬ የምንተክለው የነገን ህይወት ነው” ብለዋል።
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ማራዶና ዘለቀ በበኩላቸው፣ በዛሬው ዕለት በ8ቱም ክፍለ ከተሞች ከ220 ሺህ በላይ ችግኞች እየተተከሉ መሆኑን ገልጸው፣ ይህ ተግባር የሀዋሳ ሐይቅን ከደለል ስጋት በመጠበቅ፣ የተፈጥሮ ሀብትን በማልማት፣ የጎርፍና የድርቅ አደጋዎችን በመቀነስ እንዲሁም የምግብ ዋስትናን በማጠናከር ለማይበገር ኢኮኖሚ ግንባታ መሠረት እንደሚጥል ገልጸዋል።
የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት መምሪያ ሀላፊ አቶ ስጦታው ከንባታ ደግሞ፣ ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በሀዋሳ ከተማ ከ21.7 ሚሊዮን በላይ ችግኞች መተከላቸውንና የከተማዋ የደን ሽፋን 27.3 በመቶ መድረሱን ገልጸዋል።
ይህም የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በሀዋሳ ተጨባጭ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን ያሳያል ሲሉ ተናግረዋል።
ዘጋቢ፡ፈንታሁን መለሰ

More Stories
እንደ ሀገር ”በጋራ ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሃ-ግብር በሸካ ዞን በማሻ ማረሚያ ተቋም ተካሄደ
ችግኝ መትከል ጥሪት ለትውልድ የማስቀመጥ ተግባር በመሆኑ ለተግባራዊነቱ በቅንጅት መረባረብ እንደሚገባ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ሙስጠፋ ኢሳ ገለፁ።
በኣሪ ዞን በባካ ዳዉላ ኣሪ ወረዳ “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል የአንድ ጀምበር አረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር እየተካሄደ ይገኛል