በኣሪ ዞን በባካ ዳዉላ ኣሪ ወረዳ “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል የአንድ ጀምበር አረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር እየተካሄደ ይገኛል
በወረዳዉ በሁሉም ቀበሌያት የዘንድሮዉ የአርንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ፕሮግራም እናቶች ፣ አባቶች ፣ወጣቶች ፣ሴቶች ህፃናት በአጠቃላይ ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የነገዋን ኢትዮጵያ አረንጓዴ አካባቢን ለመፍጠር በነቂስ በመውጣት የችግኝ ተከላ ፕሮግራም እያካሄዱ ነው።
በዘንድሮዉ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ እንደ ወረዳ ጠቅላላ ስድስት መቶ ሺህ (600,000)ችግኞች ይተከላሉ ተብሎም ይጠበቃል።
በመርሃ-ግብሩም ከክልል፣ከዞን እና የወረዳ አጠቃላይ አመራሮች ባለሙያዎች፣ተፅዕኖ ፈጣሪ ወጣቶች ነገ የሀገር ተረካቢ ህፃናት ባጠቃላይ ህብረተሰቡ እየተሳተፉም ነው።
ዘጋቢ፡ ተመስገን ሰይፉ – ከጂንካ ጣቢያችን
በኣሪ ዞን በባካ ዳዉላ ኣሪ ወረዳ “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል የአንድ ጀምበር አረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር እየተካሄደ ይገኛል

More Stories
የጎፋና ኦይዳ ህዝቦች የባህል፣ የታሪክና የቋንቋ ሲምፖዚየም በሳውላ ከተማ እየተካሄደ ነው
ጥራት ያለው ቡና የአርሶ አደሮችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሚናው የጎላ መሆኑን በጌዴኦ ዞን የይርጋጨፌ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ
የግብርና ቴክኖሎጂን በማስፋት አርሶ አደሩ ለገበያ የሚተርፍ ምርት እያመረተ መሆኑ ተገለጸ