በአንድ ጀምበር 800 ሚሊየን ችግኝ ተከላ አካል የሆነው 8ኛው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ በኣሪ ዞን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ተከላ እየተካሄደ ነው

በአንድ ጀምበር 800 ሚሊየን ችግኝ ተከላ አካል የሆነው 8ኛው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ በኣሪ ዞን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ተከላ እየተካሄደ ነው

ሀዋሳ፡ ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ)በአንድ ጀንበር 800 ሚሊየን ችግኝ ተከላ አካል የሆነው 8ኛው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ በአሪ ዞን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች እየተተከሉ ይገኛሉ፡፡

“ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል ዞናዊ የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር በአሪ ዞን ጂንካ ከተማ አስተዳድር በይፋ ተጀምሯል።

የአረንጓዴ አሻራ ልማቱ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋምና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና እንዳለው የገለፁት በአሪ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አስፋው ዶሬ ናቸው።

የአሪ ዞን ግብርና መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ኤልያስ ቃሾ በተከላው መርሃ-ግብር ባስተላለፉት መልዕክት በዞኑ የደን፣ የጥምር ደን ፣የፍራፍሬ የቀርከሃ እንዲሁም ለእንስሳት መኖ የሚሆን 4 ሚሊየን 990 ሺ 246 ችግኝ በጂኦሪፈራንስ 91ቀበሌያት ላይ 879 ሄክታር መሬት በተከላው ይሸፈናል ብለዋል።

የጂንካ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ደግፌ ጌታቸው ማህበረሰቡ በነቂስ ወጥቶ የተከላቸውን ችግኞችን በአደረጃጀት ልዩ እንክብካቤ እንዲያደርጉ አሳስብዋል።

ዘጋቢ፡ ተመስገን አሰፋ – ከጂንካ ጣቢያችን