በዘንድሮ አንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር ከ 21 ሚሊዮን በላይ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች እንደሚተከሉ የጋሞ ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ

በዘንድሮ አንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር ከ 21 ሚሊዮን በላይ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች እንደሚተከሉ የጋሞ ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ

“ተስፋን እንትከል ዞናችንን በአረንጓዴ አሻራ እናልብስ” በሚል መሪ ቃል የዞኑ የአንድ ጀምበር ተከላ ማስጀመሪያ መርሐግብር በጋጮ ባባ በወረዳ እየተካሄደ ይገኛል።

በአየር ንብረት ለውጥ እጅግ ከተፈተኑ አከባቢዎች አንዱ የጋጮ ባባ ወረዳ መሆኑ የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው።

የአካባቢውን የተፈጥሮ ሀብት ለመጠበቅ፣ የደን ሽፋንን ለማስፋፋትና የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቀነስ በሚደረገው ሀገራዊ ጥረት አካል የሆነው የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ “አንድ ጀምበር ተከላ” መርሃ ግብር ታሪክ ለመድገም በጋጮ ባባ ወረዳ በሀገር ሽማግሌዎች ቡራኬ ተጀምሯል።

የጋሞ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ማጌሶ ማሾሌ በአንድ ጀምበር በዞኑ 21 ሚሊዮን 118 ሺህ 931 ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች እስከ 12 ሰዓት ይተከላል ብለዋል።

ከዚህም 2.3 ሚሊዮን ችግኞች በጋጮ ባባ ወረዳ ይተከላል ብለዋል።

የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብሩክ ቡፃ፤ በወረዳው በተሰሩ ስራዎች ተጨባጭ ለውጥ በማስመዝገብ ላይ መሆናቸውን ተናግረው ለክትትልና እንክብካቤ ስራዎች ትኩረት ይሰጣል ብለዋል።

የኢፌዴሪ ስደተኞችና ተመላሾች ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን፤ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተፈጥሮ ሀብት የታደለች መሆኗን ጠቅሰው ተፈጥሮን ካልጠበቁና ካልተንከባከቡ አደጋ ሊከሰት ስለሚችል የጋሞ አባቶች ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በቀጣይ ተመልሰው የፅድቀት መጠኑንና የእንክብካቤ ስራውን እንሚመለከቱም ገልፀዋል።

በመርሀ-ግብሩ ንግግር ያደረጉት የዕለቱ ክብር ዕንግዳ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ አለምፀሐይ ደመቀ፤ አረንጓዴ አሻራ ከተጀመረ ወዲህ በርካታ ለውጦች መምጣታቸውን ተናግረው በአካባቢው የአየር ንብረት ለውጥ ያስከተለውን ተፅእኖዎችን ለመቀልበስ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

በክልሉ በአንድ ጀምበር 69 ሚሊዮን ችግኞች እንደሚተከሉ ገልፀው የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት በቅንጅት መሰራት እንዳለበት ጥሪ አስተላልፈዋለ።

በመርሃ- ግብሩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ አለምነሽ ደመቀ፣ የጋሞ ዞን ምክትል አስተዳዳሪናሪ የስራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሐኪመ አየለ፣ የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ገዛኸኝ ጋሞ፣ የዞኑ ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ማጌሶ ማሾሌ፣ የፈዴራልና ክልል ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የወረዳው አመራሮችና ነዋሪዎች ሌሎች የመንግሥትና የማኅበረሰብ ተቋማት ተወካዮች የሀገር ሽማግሌዎች ከጧቱ 12 ጀምሮ በመውጣት በንቃት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ተከላው እስከ ማምሻው 12 ሰዓት ድረስ የሚቀጥል ይሆናል።

ዘጋቢ፡ ተነሳ ተረፈ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን