ተስፋን እንትከል የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር በሲዳማ ክልል መካሄድ ጀምሯል
ሀዋሳ፡ ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ)ተስፋን እንትከል የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር በሲዳማ ክልል ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ቦርቻ ወረዳ ሃልዳዳ ዴላ ቀበሌ በይፋ ተጀምሯል፡፡
የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ እና የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ መምህሩ ሞኬ መርሃ-ግብሩን በይፋ አስጀምረዋል፡፡
በክልሉ በአንድ ጀምበር ከ10 ሚሊየን በላይ ችግኝ እንደሚተከል የገለጹት የብልጽግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅ/ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ በዚህም ከ1,5 ሚሊየን ህዝብ በመርሃ ግብሩ ተሳታፊ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ከ2011 ጀምሮ በክልሉ በተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ተጨባጭ ለውጥ መመዝገቡንም አቶ አብርሃም ገልጸዋል፡፡
የሲደማ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ መምህሩ ሞኬ በተከላ መርሃ- ግብሩ ወቅት በክልሉ በተለዩ 243 ቦታዎች 4ሺህ 108 ሄክታር መሬት ላይ የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ እየተከናወነ ነው ብለዋል፡፡
በዘንድሮ መርሃ-ግብር የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያላቸው የፍራፍሬና የቡና ችግኞች በብዛት ተዘጋጅተው ለተከላ መቅረባቸውን የተናገሩት አቶ መምህሩ ከዚህ ቀደም በተመሣሣይ በአረንጓዴ አሻራ በተተከሉ የፍራፍሬ ችግኞች ከይርጋለም አግሮ ኢንዱስትሪ ጋር በማስተሳሰር በተሰራ ሥራ ሀገሪቱ የዉጪ ምንዛሪ ገቢ እንድታገኝ ማስቻሉን ጠቁመዋል፡፡
በአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ የተሳተፉ የአከባቢው ነዋሪዎች አቶ ከፍያለው ቶማስና አያናው በራሶ የአየር ንብረት ለውጥ ለመቋቋም የአረንጓዴ አሻራ ወሳኝ መሆኑን ተናግረው ከመትከልም ባለፍ የመንከባከብና የመጠበቅ ሀላፊነትን እንደሚወጡ ገልፀዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ታሪኩ ሰብስቤ

More Stories
እንደ ሀገር ”በጋራ ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሃ-ግብር በሸካ ዞን በማሻ ማረሚያ ተቋም ተካሄደ
ችግኝ መትከል ጥሪት ለትውልድ የማስቀመጥ ተግባር በመሆኑ ለተግባራዊነቱ በቅንጅት መረባረብ እንደሚገባ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ሙስጠፋ ኢሳ ገለፁ።
በሀዋሳ ከተማም ከ220 ሺህ በላይ ችግኞችን በ8ቱም ክፍለ ከተሞች ”ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል”እየተከለች ነው።