የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በከምባታ ዞን በይፋ ተጀመረ
በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ታሪካዊ መርሐ ግብር በይፋ የተጀመረ ሲሆን በከምባታ ዞንም ቀዲዳ ጋሜላ ወረዳ ደጋ ቀዲዳ ቀበሌ ሀሮ ተከላ ሳይት የማስጀመሪያ መርሀ ግብር ተከናውኗል።
የከምባታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አረጋ እሸቱ፣ አቶ ተሾመ ሄራሞ የዞኑ ምክትል ዋና አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ተሾመ ሄራሞ እና ሌሎችም የዞንና የወረዳ አመራሮች፣ የጸጥታ አካላት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ እናቶች፣ ወጣቶች እና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች በተገኙበት የተከላ መርሀግብሩ ተጀምሯል።
በዚህ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በዞን ደረጃ 1.6 ሚሊዮን ችግኞች ይተከላሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ለዚህም ከ486 ሄክታር በላይ መሬት ላይ በተመረጡ 44 የተከላ ቦታዎች ተከላው ይከናወናል።
ዘጋቢ: ምስጋና ኤልያስ

More Stories
ሰው ተኮር የበጎነት እሴቶች በሁሉም አካባቢዎች ተደራሽ እንዲሆኑ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ላይ ይገኛል – ዶ/ር መሀመድ ኑሪዬ
በዓልን ምክንያት በማድረግ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ እንዳይደረግ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
የጎፋና ኦይዳ ህዝቦች የባህል፣ የታሪክና የቋንቋ ሲምፖዚየም በሳውላ ከተማ እየተካሄደ ነው