የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የክልሉን መንግስት የ2019 በጀት ከ85.7 ቢሊየን ብር በላይ አፀደቀ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ ባለው 6ኛ ዙር፣ 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 7ኛ መደበኛ ጉባኤ በክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት የቀረበን የክልሉን መንግስት የ2019 ረቂቅ በጀት አስመልክቶ በጥልቀት ተወያይቷል፡፡
ምክር ቤቱ የቀረበውን የክልሉን መንግስት የ2019 ረቂቅ በጀት ሀገራዊና ክልላዊ የዘላቂ ሰላምና የሁለንተናዊ ብልፅግና ግቦችን ዕውን ለማድረግ የተጀመሩ ጥረቶችን በማጠናከር የክልሉን ሕዝብ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አንጻር በመመርመር 85 ቢሊየን 774 ሚሊዮን 12 ሺህ 25 ብር አጽድቋል።
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈሪ አባተ፤ የረቂቅ በጀቱን ዝርዝር ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።
የበጀቱን ከግማሽ በላይ በዉስጥ ገቢ የሚሰበሰብ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ተፈሪ፤ ገቢን አሟጦ በመሰብሰብ መጠቀም እና ዉስን የሆነውን ሀብት በአግባቡ ማስተዳደር እንደሚገባና በጀትን በዲጂታል መንገድ በማስተዳደር የተመደበው በጀት ለታለመው አላማ እንዲውልና ጤናማ የሆነ የፋይናንስ ስርዓት እንዲኖር እንዲሚሰራ ተናግረዋል።
ከበጀቱ 20 በመቶ ለክልል ማዕከላት እንዲሁም 80 በመቶው ለዞን አስተዳደር እርከኖች የሚዉል መሆኑ ተገልጿል።
ዘጋቢ፡ ባዬ በልስቲ

More Stories
ህዝበ ክርስቲያኑ የ2019 ዓ.ም የእንቁጣጣሽ በዓልን በሚያከብርበት ወቅት አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ የሀይማኖት አባቶች ተናገሩ
የ2018 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ታላላቅ ስኬቶችን ያስመዘገበችበት እና የዲጂታል ሽግግር የሉዓላዊነቷ ምሰሶ መሆን የቻለችበት አመት መሆኑን አቶ አልማው ዘውዴ ገለፁ
ጳጕሜን 5 “የነገው ቀን” በኮሬ ዞን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው