የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን አባላት በግብጽ አዲስ እየተገነባ ያለውን የካይሮ ከተማ ጎበኙ
ሀዋሳ፡ ሐምሌ 20/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን አባላት በግብጽ አዲስ እየተገነባ ያለውን የካይሮ ከተማ ጎብኝተዋል።
ከተለያዩ ከተሞች እና ተቋማት የተውጣጣው የልዑካን ቡድን የካይሮ ከተማን የሕዝብ ብዛት መጨናነቅ ለማስተንፈስ መልሶ የማልማት እና ለወደፊቱ ትውልድ የሚሆን ዘመናዊ፣ ሁለገብ እና ምቹ ከተማን ለመገንባት የተሠሩ ሥራዎችን ጎብኝቷል።
ጥንታዊነትን ከዘመናዊነት፤ ገጠርን ከከተማ አስማምቶ ለማደግ የተከናወኑ ተግባራትንም ተመልክቷል።
በጉብኝቱ ወቅት ከካይሮ ከተማ አስተዳደር ጋር ከተሞችን በማዘመን፣ ወቅቱን የዋጀ የከተማ እና የመሠረተ ልማት ግንባታን፣ እንዲሁም የተጨናነቁ የከተማ አካባቢዎችን ስለማስተካከል በተሰሩ ስራዎች ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል።
ኢትዮጵያና ግብጽ በባህል፣ በታሪክና በሕዝብ ብዛት ተቀራራቢነት ያላቸው በመሆኑ የልዑካን ቡድኑ ያገኘው ልምድ በየከተሞቹ ሊተገበሩ የሚችሉ መሆናቸውን አባላቱ ገልጸዋል።
ጉብኝቱ ሐምሌ 6 ቀን 2015 ዓ.ም የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ በግብጽ ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ የተከናወነ ነው።
በጉብኝቱ የፌደራል አመራሮች፣ የአዲስ አበባ፣ የአዳማ፣ የባሕር ዳርና የሐዋሳ ከንቲባዎችም ተሳትፈዋል።

More Stories
ውድና ውስን የሆነውን መሬት ያለብክነት ለመምራትና ለመጠቀም እየተሰራ ነው – የባስኬቶ ዞን አስተዳደር
በጎፋ ዞን ጋልማ ከተማ በ2019 በጀት ዓመት ከ18 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር መታቀዱ ተገለፀ
የሀድያ ብሔር የዘመን መለወጫ “ያሆዴ” በዓልን ለማክበር በቂ ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ